Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക


പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ന്നിസാഅ്   ആയത്ത്:
وَلَوۡ أَنَّا كَتَبۡنَا عَلَيۡهِمۡ أَنِ ٱقۡتُلُوٓاْ أَنفُسَكُمۡ أَوِ ٱخۡرُجُواْ مِن دِيَٰرِكُم مَّا فَعَلُوهُ إِلَّا قَلِيلٞ مِّنۡهُمۡۖ وَلَوۡ أَنَّهُمۡ فَعَلُواْ مَا يُوعَظُونَ بِهِۦ لَكَانَ خَيۡرٗا لَّهُمۡ وَأَشَدَّ تَثۡبِيتٗا
66. እኛም በእነርሱ ላይ፡- «ነፍሶቻችሁን ግደሉ» ወይም «ከአገሮቻችሁ ውጡ» ማለትን በፃፍን ኖሮ ከእነርሱ ጥቂቶቹ እንጂ ባልሰሩት (ባልተገበሩት) ነበር። የሚገሰጹበትን ነገር በተገበሩት ኖሮ ለእነርሱ መልካምና በእምነታቸው ላይ ለመርጋትም በጣም የበረታ በሆነ ነበር።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَإِذٗا لَّأٓتَيۡنَٰهُم مِّن لَّدُنَّآ أَجۡرًا عَظِيمٗا
67. ያን ጊዜ ደግሞ ከእኛ ዘንድ ታላቅን ምንዳ በሰጠናቸው ነበር።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَلَهَدَيۡنَٰهُمۡ صِرَٰطٗا مُّسۡتَقِيمٗا
68. ቀጥተኛውንም መንገድ በእርግጥ በመራናቸው ነበር::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ فَأُوْلَٰٓئِكَ مَعَ ٱلَّذِينَ أَنۡعَمَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِم مِّنَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ وَٱلصِّدِّيقِينَ وَٱلشُّهَدَآءِ وَٱلصَّٰلِحِينَۚ وَحَسُنَ أُوْلَٰٓئِكَ رَفِيقٗا
69. አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ ከእነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ፀጋውን ከዋለላቸው ከነብያት፤ ከፃድቃን፤ ከሰማዕታትና ከመልካሞቹ ጋር ይሆናሉ። የእነዚያም ጓደኝነት አማረ።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
ذَٰلِكَ ٱلۡفَضۡلُ مِنَ ٱللَّهِۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ عَلِيمٗا
70. ይህ ችሮታ ከአላህ የተለገሰ ነው:: አዋቂነትም በአላህ በቃ::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ خُذُواْ حِذۡرَكُمۡ فَٱنفِرُواْ ثُبَاتٍ أَوِ ٱنفِرُواْ جَمِيعٗا
71. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጥንቃቄያችሁን ያዙ:: ክፍልፍልም ወይም በአንድ ሆናችሁ ለዘመቻ ውጡ::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَإِنَّ مِنكُمۡ لَمَن لَّيُبَطِّئَنَّ فَإِنۡ أَصَٰبَتۡكُم مُّصِيبَةٞ قَالَ قَدۡ أَنۡعَمَ ٱللَّهُ عَلَيَّ إِذۡ لَمۡ أَكُن مَّعَهُمۡ شَهِيدٗا
72. ከናንተ ውስጥ በእርግጥ ከዘመቻ ወደ ኋላ የሚንጓደድ (የሚጎተት) ሰው አለ:: አደጋም ካገኛችሁ «ከእነርሱ ጋር ተሳታፊ ባለመሆኔ አላህ በእኔ ላይ በእርግጥ ጸጋውን ዋለልኝ።» ይላል።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَلَئِنۡ أَصَٰبَكُمۡ فَضۡلٞ مِّنَ ٱللَّهِ لَيَقُولَنَّ كَأَن لَّمۡ تَكُنۢ بَيۡنَكُمۡ وَبَيۡنَهُۥ مَوَدَّةٞ يَٰلَيۡتَنِي كُنتُ مَعَهُمۡ فَأَفُوزَ فَوۡزًا عَظِيمٗا
73. ከአላህ የሆነ ችሮታ ካገኛችሁ ደግሞ በእናንተና በእርሱ መካከል ፍቅር አንዳልነበረ ሁኖ «ታላቅ እድል አገኝ ዘንድ ምን ነው ከእነርሱ ጋር በሆንኩ?» ይላል።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
۞ فَلۡيُقَٰتِلۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ ٱلَّذِينَ يَشۡرُونَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا بِٱلۡأٓخِرَةِۚ وَمَن يُقَٰتِلۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ فَيُقۡتَلۡ أَوۡ يَغۡلِبۡ فَسَوۡفَ نُؤۡتِيهِ أَجۡرًا عَظِيمٗا
74. እናም እነዚያ ቅርቧን ህይወት በመጨረሻይቱ ሕይወት የሚለውጡ (የሚገዙ) በአላህ መንገድ ይጋደሉ:: በአላህ መንገድ የሚጋደልና ከዚያ የሚገደል ወይም የሚያሸንፍ ሁሉ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጠዋለን።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ന്നിസാഅ്
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക