Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക


പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ന്നിസാഅ്   ആയത്ത്:
ٱلرِّجَالُ قَوَّٰمُونَ عَلَى ٱلنِّسَآءِ بِمَا فَضَّلَ ٱللَّهُ بَعۡضَهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖ وَبِمَآ أَنفَقُواْ مِنۡ أَمۡوَٰلِهِمۡۚ فَٱلصَّٰلِحَٰتُ قَٰنِتَٰتٌ حَٰفِظَٰتٞ لِّلۡغَيۡبِ بِمَا حَفِظَ ٱللَّهُۚ وَٱلَّٰتِي تَخَافُونَ نُشُوزَهُنَّ فَعِظُوهُنَّ وَٱهۡجُرُوهُنَّ فِي ٱلۡمَضَاجِعِ وَٱضۡرِبُوهُنَّۖ فَإِنۡ أَطَعۡنَكُمۡ فَلَا تَبۡغُواْ عَلَيۡهِنَّ سَبِيلًاۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيّٗا كَبِيرٗا
34. ወንዶች ለሴቶች ቋሚና የበላይ አስተዳዳሪዎች ናቸው:: አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና ወንዶች ከገንዘቦቻቸው ለሴቶች በመስጠታቸው ምክኒያት ነው:: መልካሞቹ ሴቶች ማለት ለባሎቻቸው ታዛዦች፤ አላህ ባስጠበቀው ነገር ከባሎቻቸው ሩቅ የሆነውን ጠባቂዎች ናቸው:: እነዚያን ማመፃቸውን የምትፈሩትን ሴቶች መጀመሪያ ገስጿቸው:: ከዚያም በመኝታቸው ተለዩዋቸው:: ከዚያም (በአካሎቻቸው ላይ ሳካ ሳታደርሱ) ምቷቸው:: ከታዘዟችሁ ለመጨቆን ስትሉ በእነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ:: አላህ የሁሉም በላይና ታላቅ ነውና::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَإِنۡ خِفۡتُمۡ شِقَاقَ بَيۡنِهِمَا فَٱبۡعَثُواْ حَكَمٗا مِّنۡ أَهۡلِهِۦ وَحَكَمٗا مِّنۡ أَهۡلِهَآ إِن يُرِيدَآ إِصۡلَٰحٗا يُوَفِّقِ ٱللَّهُ بَيۡنَهُمَآۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا خَبِيرٗا
35. በመካከላቸውም ጭቅጭቅ መኖሩን ብትፈሩ (ብታውቁ) ከቤተሰቡና ከቤተሰቦቿ የተውጣጡ የቤተ ዘመድ ጉባኤ አዋቅሩ:: ሁለቱም እርቅን ቢሹ አላህ በመካከላቸው ያስማማቸዋል:: አላህ ግልጽንም ሆነ ውስጥንም አዋቂ ነውና::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
۞ وَٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ وَلَا تُشۡرِكُواْ بِهِۦ شَيۡـٔٗاۖ وَبِٱلۡوَٰلِدَيۡنِ إِحۡسَٰنٗا وَبِذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱلۡجَارِ ذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡجَارِ ٱلۡجُنُبِ وَٱلصَّاحِبِ بِٱلۡجَنۢبِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُكُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخۡتَالٗا فَخُورًا
36. አላህን ተገዙ:: በእርሱ ምንንም አታጋሩ። ለወላጆች፣ ለቅርብ ዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለምስኪኖች፣ ለቅርብ ጎረቤት፣ ለሩቅ ጎረቤት፣ ለጎን ባልደረባ፣ ለመንገደኛ፣ እጆቻችሁ ንብረት ላደረጓቸው ባሮች መልካምን ስሩ። አላህ ኩራተኞችንና ጉረኞችን አይወድምና::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
ٱلَّذِينَ يَبۡخَلُونَ وَيَأۡمُرُونَ ٱلنَّاسَ بِٱلۡبُخۡلِ وَيَكۡتُمُونَ مَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦۗ وَأَعۡتَدۡنَا لِلۡكَٰفِرِينَ عَذَابٗا مُّهِينٗا
37. እነዚያ የሚሰስቱ ንፉጎችና ሰዎችንም በመሰሰት (በንፍግና) የሚያዝዙ አላህ ከችሮታው የሰጣቸውን ጸጋ የሚደብቁ ብርቱን ቅጣት ይቀጣቸዋል። ለከሓዲያንም አዋራጅን ቅጣት አዘጋጅተናል።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ന്നിസാഅ്
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക