Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ന്നിസാഅ്   ആയത്ത്:
ٱلَّذِينَ يَتَرَبَّصُونَ بِكُمۡ فَإِن كَانَ لَكُمۡ فَتۡحٞ مِّنَ ٱللَّهِ قَالُوٓاْ أَلَمۡ نَكُن مَّعَكُمۡ وَإِن كَانَ لِلۡكَٰفِرِينَ نَصِيبٞ قَالُوٓاْ أَلَمۡ نَسۡتَحۡوِذۡ عَلَيۡكُمۡ وَنَمۡنَعۡكُم مِّنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۚ فَٱللَّهُ يَحۡكُمُ بَيۡنَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ وَلَن يَجۡعَلَ ٱللَّهُ لِلۡكَٰفِرِينَ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ سَبِيلًا
141. እነዚያ (አስመሳዮች) በእናንተ ላይ የጊዜ መዘዋወርን የሚጠባበቁ ናቸው:: ለእናንተም ከአላህ የሆነ አሸናፊነት ሲኖራችሁ «ከናንተ ጋር አልነበርንምን?» ይላሉ:: ለከሓዲያን እድል ሲኖር ደግሞ «ከአሁን በፊት እኛ በእናንተ ላይ አልተሾምንባችሁምና (አልተውናችሁምን?) ከአማኞች አደጋስ አልከለከልናችሁምን?» ይላሉ:: አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላችሁ ይፈርዳል:: አላህ ለከሓዲያን በአማኞች ላይ መንገድን በፍጹም አያደርግም::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِنَّ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ يُخَٰدِعُونَ ٱللَّهَ وَهُوَ خَٰدِعُهُمۡ وَإِذَا قَامُوٓاْ إِلَى ٱلصَّلَوٰةِ قَامُواْ كُسَالَىٰ يُرَآءُونَ ٱلنَّاسَ وَلَا يَذۡكُرُونَ ٱللَّهَ إِلَّا قَلِيلٗا
142. አስመሳዮች አላህን ያታልላሉ:: እርሱም አታላያቸው ነው:: ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾችና ሰዎችን የሚያሳዩ ሆነው ይቆማሉ:: አላህንም ጥቂትን እንጂ አያወሱም።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
مُّذَبۡذَبِينَ بَيۡنَ ذَٰلِكَ لَآ إِلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِ وَلَآ إِلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِۚ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ سَبِيلٗا
143. በዚህ መካከል ወላዋዮች ሆነው ይታያሉ:: ወደ እነዚህም ወደ እነዚያም አይደሉም:: አላህም ያሳሳተውን ለእርሱ የቅንነት መንገድን በፍጹም አታገኝለትም::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّخِذُواْ ٱلۡكَٰفِرِينَ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۚ أَتُرِيدُونَ أَن تَجۡعَلُواْ لِلَّهِ عَلَيۡكُمۡ سُلۡطَٰنٗا مُّبِينًا
144. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአማኞች ሌላ ከሓዲያንን ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙ:: ለአላህ በእናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃዎችን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን?
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِنَّ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ فِي ٱلدَّرۡكِ ٱلۡأَسۡفَلِ مِنَ ٱلنَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمۡ نَصِيرًا
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስመሳዮች በእርግጥ ከእሳት በታችኛዋ አዘቅት ውስጥ ናቸው:: እናም ለእነርሱ ረዳትን አታገኝላቸዉም::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُواْ وَأَصۡلَحُواْ وَٱعۡتَصَمُواْ بِٱللَّهِ وَأَخۡلَصُواْ دِينَهُمۡ لِلَّهِ فَأُوْلَٰٓئِكَ مَعَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۖ وَسَوۡفَ يُؤۡتِ ٱللَّهُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ أَجۡرًا عَظِيمٗا
146. እነዚያ የተመለሱና ስራቸውን ያሳመሩ በአላህ የተጠበቁ ሃይማኖታቸውንም ለአላህ ፍጹም ያደረጉት ሲቀሩ:: እነዚያስ ከአማኞች ጋር ናቸው:: ለአማኞችም አላህ ታላቅን ምንዳ በእርግጥ ይሰጣል::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
مَّا يَفۡعَلُ ٱللَّهُ بِعَذَابِكُمۡ إِن شَكَرۡتُمۡ وَءَامَنتُمۡۚ وَكَانَ ٱللَّهُ شَاكِرًا عَلِيمٗا
147. ብታመሰግኑና ብታምኑ አላህ እናንተን በመቅጣት ምን ያደርጋል? አላህም ወረታን መላሽ አዋቂ ነው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ന്നിസാഅ്
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക