Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക


പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ന്നിസാഅ്   ആയത്ത്:
مَّن يُطِعِ ٱلرَّسُولَ فَقَدۡ أَطَاعَ ٱللَّهَۖ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ عَلَيۡهِمۡ حَفِيظٗا
80. መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ በእርግጥ አላህን ታዘዘ:: ከትዕዛዝም የሸሸው ጉዳዩ አያሳስብህ:: በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አላክንህምና::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَيَقُولُونَ طَاعَةٞ فَإِذَا بَرَزُواْ مِنۡ عِندِكَ بَيَّتَ طَآئِفَةٞ مِّنۡهُمۡ غَيۡرَ ٱلَّذِي تَقُولُۖ وَٱللَّهُ يَكۡتُبُ مَا يُبَيِّتُونَۖ فَأَعۡرِضۡ عَنۡهُمۡ وَتَوَكَّلۡ عَلَى ٱللَّهِۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا
81. አጠገብህ ሲሆኑ የአንተ ታዛዥ ነን ይላሉ:: ካንተ ዘንድ በወጡ ጊዜ ከእነርሱ ከፊሎቹ ከዚያ በአጠገብህ ከሚሉት ሌላን በልቦቻቸው ያሳድራሉ:: አላህ በልቦቻቸው የሚያሳድሩትን ነገር ሁሉ ይጽፋል:: ስለዚህ ተዋቸውና በአላህ ላይ ብቻ ተመካ:: መመኪያነት አላህ ብቻ በቃ::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ ٱلۡقُرۡءَانَۚ وَلَوۡ كَانَ مِنۡ عِندِ غَيۡرِ ٱللَّهِ لَوَجَدُواْ فِيهِ ٱخۡتِلَٰفٗا كَثِيرٗا
82. ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ የመጣ በነበረ ኖሮ በውስጡ ብዙ መለያየትን ባገኙ ነበር::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَإِذَا جَآءَهُمۡ أَمۡرٞ مِّنَ ٱلۡأَمۡنِ أَوِ ٱلۡخَوۡفِ أَذَاعُواْ بِهِۦۖ وَلَوۡ رَدُّوهُ إِلَى ٱلرَّسُولِ وَإِلَىٰٓ أُوْلِي ٱلۡأَمۡرِ مِنۡهُمۡ لَعَلِمَهُ ٱلَّذِينَ يَسۡتَنۢبِطُونَهُۥ مِنۡهُمۡۗ وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ وَرَحۡمَتُهُۥ لَٱتَّبَعۡتُمُ ٱلشَّيۡطَٰنَ إِلَّا قَلِيلٗا
83. ሰላምን ወይም ስጋትን የሚመለከት ወሬ በመጣላቸው ጊዜ እርሱን ያሰራጫሉ (ያጋንናሉ)። ወደ መልዕክተኛውና ከእነርሱ መካከል የጉዳይ ባለቤቶች ወደ ሆኑት አዋቂዎቹ በመለሱት ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ መካከል ነገሩን በትክክል የሚረዱት ክፍሎች ባወቁት ነበር:: በእናንተ ላይ የአላህን ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከጥቂቶቹ በስተቀር ሰይጣንን በተከተላችሁ ነበር።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
فَقَٰتِلۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ لَا تُكَلَّفُ إِلَّا نَفۡسَكَۚ وَحَرِّضِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۖ عَسَى ٱللَّهُ أَن يَكُفَّ بَأۡسَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۚ وَٱللَّهُ أَشَدُّ بَأۡسٗا وَأَشَدُّ تَنكِيلٗا
84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ መንገድ ተዋጋ:: ራስህን እንጂ ሌላን አትገደድም:: አማኞችንም በአላህ መንገድ ላይ በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው:: አላህ የእነዚያን የካዱትን ሰዎች ኃይል ሊከለክል ይከጀላል:: አላህ በሃይል በመያዙ የበረታና ቅጣቱም የጠነከረ ነው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
مَّن يَشۡفَعۡ شَفَٰعَةً حَسَنَةٗ يَكُن لَّهُۥ نَصِيبٞ مِّنۡهَاۖ وَمَن يَشۡفَعۡ شَفَٰعَةٗ سَيِّئَةٗ يَكُن لَّهُۥ كِفۡلٞ مِّنۡهَاۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ مُّقِيتٗا
85. መልካም መታደግን የሚታደግ (ሽምግልናን የሚሸመግል) ሰው ሁሉ ለራሱ ከእርሷ እድል ይኖረዋል:: መጥፎ መታደግንም የሚታደግ ሰው ለእርሱ ከእርሷ ድርሻ ይኖረዋል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَإِذَا حُيِّيتُم بِتَحِيَّةٖ فَحَيُّواْ بِأَحۡسَنَ مِنۡهَآ أَوۡ رُدُّوهَآۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٍ حَسِيبًا
86.(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ሰላምታ በቀረበላችሁ ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ ሰላምታን መልሱ። ወይም እርሷኑ ራሷን መልሷት። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: ന്നിസാഅ്
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക