Check out the new design

《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 * - 译解目录

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

含义的翻译 章: 呼德   段:

ሁድ

الٓرۚ كِتَٰبٌ أُحۡكِمَتۡ ءَايَٰتُهُۥ ثُمَّ فُصِّلَتۡ مِن لَّدُنۡ حَكِيمٍ خَبِيرٍ
1.አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤. ይህ ቁርኣን አናቅጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ፤ ጥበበኛና ውስጠ አዋቂ ከሆነው (አምላክ) ዘንድ የተወረደ መጽሐፍ ነው::
阿拉伯语经注:
أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّا ٱللَّهَۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنۡهُ نَذِيرٞ وَبَشِيرٞ
2. መልዕክተኛው (እንዲህ በሚልበት ሰዎች ሆይ! ): «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ:: እኔ ለእናንተ ከእርሱ ዘንድ የተላኩ አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ።»
阿拉伯语经注:
وَأَنِ ٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ ثُمَّ تُوبُوٓاْ إِلَيۡهِ يُمَتِّعۡكُم مَّتَٰعًا حَسَنًا إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗى وَيُؤۡتِ كُلَّ ذِي فَضۡلٖ فَضۡلَهُۥۖ وَإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٖ كَبِيرٍ
3. (እንዲህም በሚልበት ሰዎች ሆይ! ): «ጌታችሁን ምህረት ለምኑት:: ከዚያ ወደ እርሱ ተመለሱ:: እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መልካምን መጥቀም ይጠቅማችኋል:: ለትሩፋት ባለቤት ሁሉ ችሮታውን (ምንዳዉን) ይሰጠዋል:: ብትሸሹም እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ::
阿拉伯语经注:
إِلَى ٱللَّهِ مَرۡجِعُكُمۡۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ
4. «መመለሻችሁ ወደ አላህ ብቻ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።»
阿拉伯语经注:
أَلَآ إِنَّهُمۡ يَثۡنُونَ صُدُورَهُمۡ لِيَسۡتَخۡفُواْ مِنۡهُۚ أَلَا حِينَ يَسۡتَغۡشُونَ ثِيَابَهُمۡ يَعۡلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعۡلِنُونَۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
5. ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ! እነርሱ ከእርሱ ከአላህ ይደበቁ ዘንድ ደረቶቻቸውን ያጥፋሉ:: ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ! ልብሶቻቸውን በሚከናነቡ ጊዜ የሚደብቁትንም ሆነ የሚገልጹትን ሁሉ ያውቃል:: እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነውና::
阿拉伯语经注:
۞ وَمَا مِن دَآبَّةٖ فِي ٱلۡأَرۡضِ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ رِزۡقُهَا وَيَعۡلَمُ مُسۡتَقَرَّهَا وَمُسۡتَوۡدَعَهَاۚ كُلّٞ فِي كِتَٰبٖ مُّبِينٖ
6. በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለና ማረፊያዋንም ሆነ መርጊያዋን የሚያውቅ ቢሆን እንጂ:: ሁሉም ነገር ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው::
阿拉伯语经注:
وَهُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ وَكَانَ عَرۡشُهُۥ عَلَى ٱلۡمَآءِ لِيَبۡلُوَكُمۡ أَيُّكُمۡ أَحۡسَنُ عَمَلٗاۗ وَلَئِن قُلۡتَ إِنَّكُم مَّبۡعُوثُونَ مِنۢ بَعۡدِ ٱلۡمَوۡتِ لَيَقُولَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٞ
7. አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ነው:: ዐርሹም በውሃ ላይ ነበር:: የትኛችሁ ስራችሁ ያማረ መሆኑ ይፈትናችሁ ዘንድ ፈጠራችሁ:: «እናንተ ከሞት በኋላ በእርግጥ ተቀስቃሾች ናችሁ» ብትልም። እነዚያ የካዱት «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።» ይላሉ::
阿拉伯语经注:
وَلَئِنۡ أَخَّرۡنَا عَنۡهُمُ ٱلۡعَذَابَ إِلَىٰٓ أُمَّةٖ مَّعۡدُودَةٖ لَّيَقُولُنَّ مَا يَحۡبِسُهُۥٓۗ أَلَا يَوۡمَ يَأۡتِيهِمۡ لَيۡسَ مَصۡرُوفًا عَنۡهُمۡ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
8. ቅጣቱንም ለተቆጠሩ ጥቂት ጊዜያቶች ብናቆይላቸው «ከመውረድ የሚከለክለው ምንድን ነው?» ይላሉ:: ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ:: በሚመጣባቸው ቀን ከእነርሱ ላይ ተመላሽ አይደለም:: በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩትም ቅጣት በእነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል::
阿拉伯语经注:
وَلَئِنۡ أَذَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ مِنَّا رَحۡمَةٗ ثُمَّ نَزَعۡنَٰهَا مِنۡهُ إِنَّهُۥ لَيَـُٔوسٞ كَفُورٞ
9. ሰውንም ከችሮታችን ብናቀምሰውና ከዚያ ብንወስድበት እርሱ ተስፋ ቆራጭና ክህደተ ብርቱ ነው::
阿拉伯语经注:
وَلَئِنۡ أَذَقۡنَٰهُ نَعۡمَآءَ بَعۡدَ ضَرَّآءَ مَسَّتۡهُ لَيَقُولَنَّ ذَهَبَ ٱلسَّيِّـَٔاتُ عَنِّيٓۚ إِنَّهُۥ لَفَرِحٞ فَخُورٌ
10. ካገኘችዉም ችግር በኋላ ጸጋዎቻችንን ብናቀምሰው «ችግሮች ከእኔ ላይ ተወገዱ።» ይላል:: አያመሰግንም:: እርሱ ተደሳችና ጉረኛ ነውና::
阿拉伯语经注:
إِلَّا ٱلَّذِينَ صَبَرُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَأَجۡرٞ كَبِيرٞ
11. እነዚያ የታገሱና መልካም ሥራዎችንም የሰሩ ሁሉ እነዚያ ለእነርሱ ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው::
阿拉伯语经注:
فَلَعَلَّكَ تَارِكُۢ بَعۡضَ مَا يُوحَىٰٓ إِلَيۡكَ وَضَآئِقُۢ بِهِۦ صَدۡرُكَ أَن يَقُولُواْ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ كَنزٌ أَوۡ جَآءَ مَعَهُۥ مَلَكٌۚ إِنَّمَآ أَنتَ نَذِيرٞۚ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ وَكِيلٌ
12. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይ (የሀብት) ድልብ ለምን አልተወረደም? ወይም ከእርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም?» ማለታቸውን በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በእርሱም ልብህ ጠባብ ሊሆን ይፈራልሃል:: አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ (ወኪል) ተጠባባቂ ነው::
阿拉伯语经注:
أَمۡ يَقُولُونَ ٱفۡتَرَىٰهُۖ قُلۡ فَأۡتُواْ بِعَشۡرِ سُوَرٖ مِّثۡلِهِۦ مُفۡتَرَيَٰتٖ وَٱدۡعُواْ مَنِ ٱسۡتَطَعۡتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም «ቁርኣንን ቀጣጠፈው» ይላሉን? «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን አስር የተቀጣጠፉ ምዕራፎች እስቲ አምጡ:: ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ረዳት ጥሩ።» በላቸው።
阿拉伯语经注:
فَإِلَّمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَكُمۡ فَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّمَآ أُنزِلَ بِعِلۡمِ ٱللَّهِ وَأَن لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ فَهَلۡ أَنتُم مُّسۡلِمُونَ
14. ለእናንተ ምላሽ ካልሰጧችሁ «(ጣዖት አምላኪያን ሆይ!) የተወረደው በአላህ እውቀት ብቻ መሆኑንና ከእርሱ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም እወቁ:: እናም አትሰልሙምን?» በላቸው።
阿拉伯语经注:
مَن كَانَ يُرِيدُ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيۡهِمۡ أَعۡمَٰلَهُمۡ فِيهَا وَهُمۡ فِيهَا لَا يُبۡخَسُونَ
15. ቅርቢቱን ህይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሁሉ ሥራዎቻቸውን ምንዳዋን በእርሷ ውስጥ ወደ እነርሱ እንሞላላቸዋለን:: እነርሱም በእርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸዉም::
阿拉伯语经注:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَيۡسَ لَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ إِلَّا ٱلنَّارُۖ وَحَبِطَ مَا صَنَعُواْ فِيهَا وَبَٰطِلٞ مَّا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
16. እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከእሳት በስተቀር የሌላቸው ናቸው:: የሰሩትም ሥራ በእርሷ ውስጥ ተበላሸ:: በቅርቢቱ ዓለም ይሰሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው::
阿拉伯语经注:
أَفَمَن كَانَ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّهِۦ وَيَتۡلُوهُ شَاهِدٞ مِّنۡهُ وَمِن قَبۡلِهِۦ كِتَٰبُ مُوسَىٰٓ إِمَامٗا وَرَحۡمَةًۚ أُوْلَٰٓئِكَ يُؤۡمِنُونَ بِهِۦۚ وَمَن يَكۡفُرۡ بِهِۦ مِنَ ٱلۡأَحۡزَابِ فَٱلنَّارُ مَوۡعِدُهُۥۚ فَلَا تَكُ فِي مِرۡيَةٖ مِّنۡهُۚ إِنَّهُ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤۡمِنُونَ
17. ከጌታው ዘንድ አስረጅ የደረሰውንና ከእርሱም የሆነ መስካሪ የሚከተለው ከቁርኣን በፊትም ለሙሳ መጽሐፍ መሪና እዝነት ሲሆን የመሰከረለት (ሰውና) የቅርቢቱን ህይወት እንደሚሻው (ሰው) ነውን? እነዚያ በእርሱ (ቁርኣን) ያምናሉ:: ከአህዛቦቹ በእርሱ የሚክድ ሰው ሁሉ መመለሻው እሳት ናት:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእርሱም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: እሱ ከጌታህ ዘንድ የሆነ እውነት ነው:: ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም::
阿拉伯语经注:
وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ يُعۡرَضُونَ عَلَىٰ رَبِّهِمۡ وَيَقُولُ ٱلۡأَشۡهَٰدُ هَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ كَذَبُواْ عَلَىٰ رَبِّهِمۡۚ أَلَا لَعۡنَةُ ٱللَّهِ عَلَى ٱلظَّٰلِمِينَ
18. በአላህ ላይ ውሸትን ከሚቀጣጥፍ ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ በጌታቸው ላይ ይቀረባሉ:: መስካሪዎቹም «እነዚህ በጌታቸው ላይ የዋሹት ናቸው።» ይላሉ:: «አስተዉሉ! የአላህ እርግማን በበዳዮች ላይ ብቻ ይሁን።» ይባላል።
阿拉伯语经注:
ٱلَّذِينَ يَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَيَبۡغُونَهَا عِوَجٗا وَهُم بِٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ كَٰفِرُونَ
19. እነርሱም እነዚያ ከአላህ መንገድ ሰዎችን የሚከለክሉ የአላህን መንገድ መጥመሟንም የሚሹት ናቸው:: እነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከሓዲያን ናቸው።
阿拉伯语经注:
أُوْلَٰٓئِكَ لَمۡ يَكُونُواْ مُعۡجِزِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا كَانَ لَهُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِنۡ أَوۡلِيَآءَۘ يُضَٰعَفُ لَهُمُ ٱلۡعَذَابُۚ مَا كَانُواْ يَسۡتَطِيعُونَ ٱلسَّمۡعَ وَمَا كَانُواْ يُبۡصِرُونَ
20. እነዚያም በምድር ውስጥ ከአላህ የሚያመልጡ አልነበሩም:: ከአላህ ሌላ ለእነርሱ ረዳቶች አልነበሯቸዉም:: ለእነርሱ ቅጣቱ ይደራረብላቸዋል:: እውነትን መስማትን የሚችሉ አልነበሩም:: የሚያዩም አልነበሩም::
阿拉伯语经注:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
21. እነዚያ እነርሱ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩና ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር የጠፋባቸው ናቸው::
阿拉伯语经注:
لَا جَرَمَ أَنَّهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ هُمُ ٱلۡأَخۡسَرُونَ
22. እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም በጣም ከሳሪዎቹ ለመሆናቸው ጥርጥር የለዉም።
阿拉伯语经注:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَأَخۡبَتُوٓاْ إِلَىٰ رَبِّهِمۡ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
23. እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ወደ ጌታቸዉም የተዋረዱት እነዚያ የገነት ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው::
阿拉伯语经注:
۞ مَثَلُ ٱلۡفَرِيقَيۡنِ كَٱلۡأَعۡمَىٰ وَٱلۡأَصَمِّ وَٱلۡبَصِيرِ وَٱلسَّمِيعِۚ هَلۡ يَسۡتَوِيَانِ مَثَلًاۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
24. የሁለቱ ክፍሎች ምሳሌ አይኑ የማያይ አይነ ስውር፤ ጆሮው የማይሰማ ደንቆሮ ሰውና አይኑ የሚያይ ጆሮው የሚሰማ ሰው ብጤ ነው:: ሁለቱ በምሳሌነት ይስተካከላሉን? አትገሰጹንም?
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوۡمِهِۦٓ إِنِّي لَكُمۡ نَذِيرٞ مُّبِينٌ
25. ኑሕን ወደ ህዝቦቹ ላክንና አላቸዉም: «እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ ነኝ።
阿拉伯语经注:
أَن لَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّا ٱللَّهَۖ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ أَلِيمٖ
26. «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ። እኔ ለእናንተ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና።»
阿拉伯语经注:
فَقَالَ ٱلۡمَلَأُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَوۡمِهِۦ مَا نَرَىٰكَ إِلَّا بَشَرٗا مِّثۡلَنَا وَمَا نَرَىٰكَ ٱتَّبَعَكَ إِلَّا ٱلَّذِينَ هُمۡ أَرَاذِلُنَا بَادِيَ ٱلرَّأۡيِ وَمَا نَرَىٰ لَكُمۡ عَلَيۡنَا مِن فَضۡلِۭ بَلۡ نَظُنُّكُمۡ كَٰذِبِينَ
27. ከህዝቦቹም መካከል እነዚያ የካዱት መሪዎች «ብጤያችን ሰው ሆነህ እንጂ አናይህም:: እነዚያም እነርሱ ሐሳበ ጥሬዎች የሆኑት ወራዶቻችን እንጂ ሌላ ተከትሎህ አናይህም:: ለእናንተም በእኛ ላይ ምንም ብልጫን አናይም:: ከቶውንም ውሸታሞች መሆናችሁን እንጠረጥራችኋለን።» አሉ።
阿拉伯语经注:
قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَءَاتَىٰنِي رَحۡمَةٗ مِّنۡ عِندِهِۦ فَعُمِّيَتۡ عَلَيۡكُمۡ أَنُلۡزِمُكُمُوهَا وَأَنتُمۡ لَهَا كَٰرِهُونَ
28. እርሱም አላቸው: «ህዝቦቼ ሆይ! እስቲ ንገሩኝ ከጌታዬ በግልጽ ማስረጃ ላይ ሆኜ ከእርሱም ዘንድ የሆነን ችሮታ ነብይነት ቢሰጠኝና በእናንተ ላይ ግን ይህች እውነታ ብትደበቅባችሁ እናንተ ለእርሷ ጠይዎች ስትሆኑ እርሷን በመቀበል እናስገድዳችኋለንን?
阿拉伯语经注:
وَيَٰقَوۡمِ لَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ مَالًاۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِۚ وَمَآ أَنَا۠ بِطَارِدِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْۚ إِنَّهُم مُّلَٰقُواْ رَبِّهِمۡ وَلَٰكِنِّيٓ أَرَىٰكُمۡ قَوۡمٗا تَجۡهَلُونَ
29. «ህዝቦቼ ሆይ! በእርሱ የተላክሁበትን በማድረስ ላይ ገንዘብን አልጠይቃችሁም:: ምንዳዬ ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም:: እኔም እነዚያን በአላህ ያመኑትን ከአጠገቤ አባራሪ አይደለሁም:: እነርሱ ከጌታቸው ጋር የሚገናኙ ናቸውና:: ግን እኔም የምትሳሳቱ ህዝቦች ሆናችሁ አያችኋለሁ::
阿拉伯语经注:
وَيَٰقَوۡمِ مَن يَنصُرُنِي مِنَ ٱللَّهِ إِن طَرَدتُّهُمۡۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
30. «ህዝቦቼ ሆይ! ባባርራቸው ከአላህ ቅጣት የሚያድነኝ ማን ነው? አትገሰጹምን?
阿拉伯语经注:
وَلَآ أَقُولُ لَكُمۡ عِندِي خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعۡلَمُ ٱلۡغَيۡبَ وَلَآ أَقُولُ إِنِّي مَلَكٞ وَلَآ أَقُولُ لِلَّذِينَ تَزۡدَرِيٓ أَعۡيُنُكُمۡ لَن يُؤۡتِيَهُمُ ٱللَّهُ خَيۡرًاۖ ٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا فِيٓ أَنفُسِهِمۡ إِنِّيٓ إِذٗا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
31. «ለናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አሉ:: ሩቅንም አውቃለሁ አልላችሁም:: እኔም መልአክ ነኝ አልላችሁም:: ለእነዚያም ዓይኖቻችሁ ለሚያዋርዷቸው አላህ ደግ ነገርን እምነትን አይሰጣቸዉም አልልም:: አላህ በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገር አዋቂ ነው:: እኔ ያን ጊዜ ከበደለኞች እሆናለሁና።» አላቸው።
阿拉伯语经注:
قَالُواْ يَٰنُوحُ قَدۡ جَٰدَلۡتَنَا فَأَكۡثَرۡتَ جِدَٰلَنَا فَأۡتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
32. «ኑህ ሆይ! በእርግጥ ተከራከርከን:: እኛን መከራከርህንም አበዛህ:: ከእውነተኞቹም ከሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው እስቲ።» አሉ።
阿拉伯语经注:
قَالَ إِنَّمَا يَأۡتِيكُم بِهِ ٱللَّهُ إِن شَآءَ وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ
33. አላቸውም: «እርሱን የሚያመጣባችሁ አላህ የፈለገ ከሆነ ብቻ ነው። እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም።
阿拉伯语经注:
وَلَا يَنفَعُكُمۡ نُصۡحِيٓ إِنۡ أَرَدتُّ أَنۡ أَنصَحَ لَكُمۡ إِن كَانَ ٱللَّهُ يُرِيدُ أَن يُغۡوِيَكُمۡۚ هُوَ رَبُّكُمۡ وَإِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
34. «እናንተም አላህ ሊያጠማችሁ ፈልጎ ከሆነ ልመክራችሁ ብፈልግም ምክሬ አይጠቅማችሁም:: እርሱ ጌታችሁ ነው:: ወደ እርሱም ብቻ ትመለሳላችሁ።» አላቸው።
阿拉伯语经注:
أَمۡ يَقُولُونَ ٱفۡتَرَىٰهُۖ قُلۡ إِنِ ٱفۡتَرَيۡتُهُۥ فَعَلَيَّ إِجۡرَامِي وَأَنَا۠ بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُجۡرِمُونَ
35. ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን? (ሙሐመድ ሆይ) «ብቀጥፈው ኃጢአቴ ቅጣቱ በእኔ ላይ ነው:: እኔም ከምታጠፉት ጥፋት ሁሉ ንጹህ ነኝ።» በላቸው።
阿拉伯语经注:
وَأُوحِيَ إِلَىٰ نُوحٍ أَنَّهُۥ لَن يُؤۡمِنَ مِن قَوۡمِكَ إِلَّا مَن قَدۡ ءَامَنَ فَلَا تَبۡتَئِسۡ بِمَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ
36. ወደ ኑህም (እንዲህ በሚል) ተወረደ: «እነሆ ከህዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር ወደፊት ሌሎች አያምኑም:: ይሠሩትም በነበሩት ክህደት አትዘን።
阿拉伯语经注:
وَٱصۡنَعِ ٱلۡفُلۡكَ بِأَعۡيُنِنَا وَوَحۡيِنَا وَلَا تُخَٰطِبۡنِي فِي ٱلَّذِينَ ظَلَمُوٓاْ إِنَّهُم مُّغۡرَقُونَ
37. «በጥበቃችንና በትዕዛዛችን ሆነህ መርከቢቱን ሥራ። በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታናግረኝ። እነርሱ በእርግጥ የሚሰምጡ ናቸውና።» አለው።
阿拉伯语经注:
وَيَصۡنَعُ ٱلۡفُلۡكَ وَكُلَّمَا مَرَّ عَلَيۡهِ مَلَأٞ مِّن قَوۡمِهِۦ سَخِرُواْ مِنۡهُۚ قَالَ إِن تَسۡخَرُواْ مِنَّا فَإِنَّا نَسۡخَرُ مِنكُمۡ كَمَا تَسۡخَرُونَ
38. ከወገኖቹም መሪዎቹ በእርሱ አጠገብ ባለፉ ቁጥር በእርሱ ላይ እየተሳለቁበት መርከቢቱን ይሠራል። አላቸውም: «በእኛ ብትሳለቁ እኛም እንደተሳለቃችሁብን በእናንተ እንሳለቅባችኋለን።
阿拉伯语经注:
فَسَوۡفَ تَعۡلَمُونَ مَن يَأۡتِيهِ عَذَابٞ يُخۡزِيهِ وَيَحِلُّ عَلَيۡهِ عَذَابٞ مُّقِيمٌ
39. «የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትን በእርሱም ላይ ዘውታሪ ቅጣት የሚሰፍርበትን ማንነት ወደ ፊት ታውቃላችሁ።» አላቸው።
阿拉伯语经注:
حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَمۡرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ قُلۡنَا ٱحۡمِلۡ فِيهَا مِن كُلّٖ زَوۡجَيۡنِ ٱثۡنَيۡنِ وَأَهۡلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيۡهِ ٱلۡقَوۡلُ وَمَنۡ ءَامَنَۚ وَمَآ ءَامَنَ مَعَهُۥٓ إِلَّا قَلِيلٞ
40. ትዕዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በመርከቧ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት (ወንድና ሴት) ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን።» አልነው:: ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም ነበር::
阿拉伯语经注:
۞ وَقَالَ ٱرۡكَبُواْ فِيهَا بِسۡمِ ٱللَّهِ مَجۡر۪ىٰهَا وَمُرۡسَىٰهَآۚ إِنَّ رَبِّي لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ
41. «‹መሄዷም መቆሟም በአላህ ስም ነው።› እያላችሁ በእርሷ ተሳፈሩ:: ጌታዬ መሓሪና አዛኝ ነውና።» አላቸው።
阿拉伯语经注:
وَهِيَ تَجۡرِي بِهِمۡ فِي مَوۡجٖ كَٱلۡجِبَالِ وَنَادَىٰ نُوحٌ ٱبۡنَهُۥ وَكَانَ فِي مَعۡزِلٖ يَٰبُنَيَّ ٱرۡكَب مَّعَنَا وَلَا تَكُن مَّعَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
42. እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ እነርሱን ይዛቸው የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት።) ኑህም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከእኛ ጋር ተሳፈር። ከከሓዲያንም አትሁን።» ሲል ጠራው።
阿拉伯语经注:
قَالَ سَـَٔاوِيٓ إِلَىٰ جَبَلٖ يَعۡصِمُنِي مِنَ ٱلۡمَآءِۚ قَالَ لَا عَاصِمَ ٱلۡيَوۡمَ مِنۡ أَمۡرِ ٱللَّهِ إِلَّا مَن رَّحِمَۚ وَحَالَ بَيۡنَهُمَا ٱلۡمَوۡجُ فَكَانَ مِنَ ٱلۡمُغۡرَقِينَ
43. ልጁም «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ።» አለ:: አባቱም «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም:: እርሱ ብቻ ያዘነለት ካልሆነ በስተቀር።» አለው:: ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ:: ልጁም ከሰማጮች ሆነ::
阿拉伯语经注:
وَقِيلَ يَٰٓأَرۡضُ ٱبۡلَعِي مَآءَكِ وَيَٰسَمَآءُ أَقۡلِعِي وَغِيضَ ٱلۡمَآءُ وَقُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ وَٱسۡتَوَتۡ عَلَى ٱلۡجُودِيِّۖ وَقِيلَ بُعۡدٗا لِّلۡقَوۡمِ ٱلظَّٰلِمِينَ
44. ተባለም «ምድር ሆይ! ዉሃሽን ዋጪ:: ሰማይ ሆይ! ዝናብሽን ያዢ።» ውሃዉም ሠረገ:: ቅጣቱም ተፈጸመ:: ጁዲይ በሚባለም ተራራ ላይ መርከቢቱ ተደላደለች:: «ለከሓዲያን ጥፋት ተገባቸው (ጥፉ)።» ተባለ።
阿拉伯语经注:
وَنَادَىٰ نُوحٞ رَّبَّهُۥ فَقَالَ رَبِّ إِنَّ ٱبۡنِي مِنۡ أَهۡلِي وَإِنَّ وَعۡدَكَ ٱلۡحَقُّ وَأَنتَ أَحۡكَمُ ٱلۡحَٰكِمِينَ
45. ኑህም ጌታውን- «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ አንዱ ነው:: ቃል ኪዳንህም እውነት ነው:: አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነህ።» በማለት ጠየቀ (ተጣራ)::
阿拉伯语经注:
قَالَ يَٰنُوحُ إِنَّهُۥ لَيۡسَ مِنۡ أَهۡلِكَۖ إِنَّهُۥ عَمَلٌ غَيۡرُ صَٰلِحٖۖ فَلَا تَسۡـَٔلۡنِ مَا لَيۡسَ لَكَ بِهِۦ عِلۡمٌۖ إِنِّيٓ أَعِظُكَ أَن تَكُونَ مِنَ ٱلۡجَٰهِلِينَ
46. አላህም «ኑህ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም:: እርሱ መልካም ያልሆነ ስራ ነው:: በእርሱ እውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ:: እኔ ከአላዋቂዎች እንዳትሆን እገስጽሃለሁ።» አለው::
阿拉伯语经注:
قَالَ رَبِّ إِنِّيٓ أَعُوذُ بِكَ أَنۡ أَسۡـَٔلَكَ مَا لَيۡسَ لِي بِهِۦ عِلۡمٞۖ وَإِلَّا تَغۡفِرۡ لِي وَتَرۡحَمۡنِيٓ أَكُن مِّنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ
47. «ጌታዬ ሆይ! በእርሱ ለእኔ እውቀት የሌለኝን ነገር የምጠይቅህ ከመሆን እኔ ባንተ እጠበቃለሁ:: ለእኔም ባትምረኝና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎቹ እሆናለሁ።» አለ።
阿拉伯语经注:
قِيلَ يَٰنُوحُ ٱهۡبِطۡ بِسَلَٰمٖ مِّنَّا وَبَرَكَٰتٍ عَلَيۡكَ وَعَلَىٰٓ أُمَمٖ مِّمَّن مَّعَكَۚ وَأُمَمٞ سَنُمَتِّعُهُمۡ ثُمَّ يَمَسُّهُم مِّنَّا عَذَابٌ أَلِيمٞ
48. «ኑህ ሆይ! ከእኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ህዝቦች ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ወደ ምድር ውረድ:: ከነሱው ዘሮች የሆኑ ህዝቦችም በቅርቢቱ ዓለም በእርግጥ እናስመቻቸዋለን:: ከዚያም ከእኛ የሆነ አሳማሚ ቅጣት ይደርስባቸዋል።» ተባለ።
阿拉伯语经注:
تِلۡكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ ٱلۡغَيۡبِ نُوحِيهَآ إِلَيۡكَۖ مَا كُنتَ تَعۡلَمُهَآ أَنتَ وَلَا قَوۡمُكَ مِن قَبۡلِ هَٰذَاۖ فَٱصۡبِرۡۖ إِنَّ ٱلۡعَٰقِبَةَ لِلۡمُتَّقِينَ
49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ዘገባ ከሩቁ ወሬዎች መካከል ወደ አንተ ያወረድነው ነው:: አንተም ሆንክ ህዝቦችህ ከዚህ በፊት የምታውቁት አልነበራችሁም:: ታገሥ ምስጉን የሆነችው ፍጻሜ ለሚጠነቀቁት ብቻ ናትና::
阿拉伯语经注:
وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمۡ هُودٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥٓۖ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا مُفۡتَرُونَ
50. ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን:: አላቸው፡ «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም:: እናንተ ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም::
阿拉伯语经注:
يَٰقَوۡمِ لَآ أَسۡـَٔلُكُمۡ عَلَيۡهِ أَجۡرًاۖ إِنۡ أَجۡرِيَ إِلَّا عَلَى ٱلَّذِي فَطَرَنِيٓۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ
51. «ህዝቦቼ ሆይ! በእርሱ (በማድረሴ) ላይም ምንዳን አልጠይቃችሁም:: ምንዳዬ በዚያ በፈጠረኝ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይደለም:: አታውቁምን?
阿拉伯语经注:
وَيَٰقَوۡمِ ٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ ثُمَّ تُوبُوٓاْ إِلَيۡهِ يُرۡسِلِ ٱلسَّمَآءَ عَلَيۡكُم مِّدۡرَارٗا وَيَزِدۡكُمۡ قُوَّةً إِلَىٰ قُوَّتِكُمۡ وَلَا تَتَوَلَّوۡاْ مُجۡرِمِينَ
52. «ህዝቦቼ ሆይ! ጌታችሁን ምህረትን ለምኑት:: ከዚያ ወደ እርሱ ተጸጸቱ:: ዝናብን በእናንተ ላይ ተከታታይ አድርጎ ይልክላችኋልና:: ወደ ኃይላችሁም ሀይልን ይጨምርላችኋል:: አመጸኞችም ሆናችሁ አትሽሹ::»
阿拉伯语经注:
قَالُواْ يَٰهُودُ مَا جِئۡتَنَا بِبَيِّنَةٖ وَمَا نَحۡنُ بِتَارِكِيٓ ءَالِهَتِنَا عَن قَوۡلِكَ وَمَا نَحۡنُ لَكَ بِمُؤۡمِنِينَ
53. እነርሱም አሉ፡- «ሁድ ሆይ! በአስረጂ አልመጣህልንም:: እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም:: እኛም ላንተ ትክክለኛ አማኞች አይደለንም።
阿拉伯语经注:
إِن نَّقُولُ إِلَّا ٱعۡتَرَىٰكَ بَعۡضُ ءَالِهَتِنَا بِسُوٓءٖۗ قَالَ إِنِّيٓ أُشۡهِدُ ٱللَّهَ وَٱشۡهَدُوٓاْ أَنِّي بَرِيٓءٞ مِّمَّا تُشۡرِكُونَ
54. «ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በክፉ ነገር በዕብደት ለክፈውሃል እንጂ ሌላን አንልም።» አሉ:: እርሱም አላቸው: «እኔ አላህን አስመሰክራለሁ:: ከምታጋሩትም እኔ ንጹህ መሆኔን መስክሩ።
阿拉伯语经注:
مِن دُونِهِۦۖ فَكِيدُونِي جَمِيعٗا ثُمَّ لَا تُنظِرُونِ
55. «ከእርሱ ሌላ አማልክትን ከምታጋሩት ንጹህ ነኝ። ሁላችሁም ሆናችሁ ተንኮልን ሥሩብኝ ከዚያ አታቆዩኝ።
阿拉伯语经注:
إِنِّي تَوَكَّلۡتُ عَلَى ٱللَّهِ رَبِّي وَرَبِّكُمۚ مَّا مِن دَآبَّةٍ إِلَّا هُوَ ءَاخِذُۢ بِنَاصِيَتِهَآۚ إِنَّ رَبِّي عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
56. «እኔ ጌታዬና ጌታችሁ በሆነው በአላህ ላይ ብቻ ተመካሁ:: በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም እርሱ አናትዋን የያዛት ብትሆን እንጂ:: ጌታዬ (ቃሉም ሥራዉም) በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነው።
阿拉伯语经注:
فَإِن تَوَلَّوۡاْ فَقَدۡ أَبۡلَغۡتُكُم مَّآ أُرۡسِلۡتُ بِهِۦٓ إِلَيۡكُمۡۚ وَيَسۡتَخۡلِفُ رَبِّي قَوۡمًا غَيۡرَكُمۡ وَلَا تَضُرُّونَهُۥ شَيۡـًٔاۚ إِنَّ رَبِّي عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٍ حَفِيظٞ
57. «ብትዞሩም ወደ እናንተ የተላኩበትን ነገር በእርግጥ አድርሼላችኋለሁ:: ጌታዬም ሌላን ህዝብ ይተካል:: ምንም አትጎዱትም:: ጌታዬ በሁሉ ነገር ላይ ተጠባባቂ ነውና።» አላቸው::
阿拉伯语经注:
وَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا نَجَّيۡنَا هُودٗا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَنَجَّيۡنَٰهُم مِّنۡ عَذَابٍ غَلِيظٖ
58. ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሁድንና እነዚያን ከእሱጋ ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን:: ከብርቱ ቅጣትም አዳናቸው::
阿拉伯语经注:
وَتِلۡكَ عَادٞۖ جَحَدُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ وَعَصَوۡاْ رُسُلَهُۥ وَٱتَّبَعُوٓاْ أَمۡرَ كُلِّ جَبَّارٍ عَنِيدٖ
59. ይህ ነገድ ዓድ ነው:: በጌታቸው ታዐምራት ካዱ:: መልዕክተኞቹንም አመጹ:: የኃያል ሞገደኛን ሁሉ ትዕዛዝም ተከተሉ::
阿拉伯语经注:
وَأُتۡبِعُواْ فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا لَعۡنَةٗ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ أَلَآ إِنَّ عَادٗا كَفَرُواْ رَبَّهُمۡۗ أَلَا بُعۡدٗا لِّعَادٖ قَوۡمِ هُودٖ
60. በዚች በቅርቢቱ ዓለምም እርግማን እንዲከተላቸው ተደረጉ:: በትንሳኤም ቀን እንደዚሁ:: አስተውሉ! ዓዶች ጌታቸውን ካዱ። አስተውሉ! የሁድ ህዝቦች ለሆኑት ዓዶች ከእዝነት መራቅ ይገባቸው::
阿拉伯语经注:
۞ وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمۡ صَٰلِحٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ وَٱسۡتَعۡمَرَكُمۡ فِيهَا فَٱسۡتَغۡفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوٓاْ إِلَيۡهِۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٞ مُّجِيبٞ
61. ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን። «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ:: ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም:: እርሱ በምድር ፈጠራችሁ:: በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ:: ምህረቱንም ለምኑት:: ከዚያም ወደ እርሱ ተመለሱ:: ጌታዬ ለሁሉም ቅርብና ለለመነው ተቀባይ ነውና።» አላቸው።
阿拉伯语经注:
قَالُواْ يَٰصَٰلِحُ قَدۡ كُنتَ فِينَا مَرۡجُوّٗا قَبۡلَ هَٰذَآۖ أَتَنۡهَىٰنَآ أَن نَّعۡبُدَ مَا يَعۡبُدُ ءَابَآؤُنَا وَإِنَّنَا لَفِي شَكّٖ مِّمَّا تَدۡعُونَآ إِلَيۡهِ مُرِيبٖ
62. እነርሱም «ሷሊህ ሆይ! ከዚህ በፊት በእኛ ውስጥ መሪ ልትሆን በእርግጥ የምትከጀል የነበርክ ስትሆን:: አባቶቻችን የሚገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን? እኛም ወደሱ ከምትጠራን ነገር በእርግጥ አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ነን።» አሉ።
阿拉伯语经注:
قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَءَاتَىٰنِي مِنۡهُ رَحۡمَةٗ فَمَن يَنصُرُنِي مِنَ ٱللَّهِ إِنۡ عَصَيۡتُهُۥۖ فَمَا تَزِيدُونَنِي غَيۡرَ تَخۡسِيرٖ
63. ሷሊህም አለ: «ህዝቦቼ ሆይ! እስቲ ንገሩኝ ከጌታዬ በሆነ ማስረጃ ላይ ሆኜ ከእርሱም የሆነን ችሮታ ነብይነት ቢሰጠኝና ባልታዘዘው ከአላህ ቅጣት የሚያድነኝ ማነው? ከማጥፋትም በስተቀር ምንም አትጨምሩልኝም።
阿拉伯语经注:
وَيَٰقَوۡمِ هَٰذِهِۦ نَاقَةُ ٱللَّهِ لَكُمۡ ءَايَةٗۖ فَذَرُوهَا تَأۡكُلۡ فِيٓ أَرۡضِ ٱللَّهِۖ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوٓءٖ فَيَأۡخُذَكُمۡ عَذَابٞ قَرِيبٞ
64. «ህዝቦቼ ሆይ! ይህች ለእናንተ ታዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናት:: ተዋትም በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ:: በክፉም አትንኳት። ቅርብ የሆነ ቅጣት ያገኛችኋልና።» አለ።
阿拉伯语经注:
فَعَقَرُوهَا فَقَالَ تَمَتَّعُواْ فِي دَارِكُمۡ ثَلَٰثَةَ أَيَّامٖۖ ذَٰلِكَ وَعۡدٌ غَيۡرُ مَكۡذُوبٖ
65. ወግተው ገደሏትም ሷሊህም «በሀገራችሁም ሶስትን ቀናት ብቻ ተጠቀሙ ይህ የማይዋሽ ቀጠሮ ነው።» አላቸው::
阿拉伯语经注:
فَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا نَجَّيۡنَا صَٰلِحٗا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَمِنۡ خِزۡيِ يَوۡمِئِذٍۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ ٱلۡقَوِيُّ ٱلۡعَزِيزُ
66. እናም ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሷሊህንና እነዚያን ከእሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት አዳንን:: ከዚያም ቀን ውርደት አዳንናቸው:: ጌታህ ብርቱውና ሁሉን አሸናፊው ነውና::
阿拉伯语经注:
وَأَخَذَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ ٱلصَّيۡحَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دِيَٰرِهِمۡ جَٰثِمِينَ
67. እነዚያን የበደሉትንም ከባድ ጩኸት ያዛቸው:: በየቤቶቻቸዉም ውስጥ የተንበረከኩ ሙት በድን ሆነው አደሩ(አነጉ)::
阿拉伯语经注:
كَأَن لَّمۡ يَغۡنَوۡاْ فِيهَآۗ أَلَآ إِنَّ ثَمُودَاْ كَفَرُواْ رَبَّهُمۡۗ أَلَا بُعۡدٗا لِّثَمُودَ
68. በእርሷ ውስጥ እንዳልኖሩ ሆኑ:: አስተውሉ! ሠሙዶች ጌታቸውን በእርግጥ ካዱ:: አስተውሉ! ለሠሙዶች ከአላህ እዝነት መራቅ ተገባቸው::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ جَآءَتۡ رُسُلُنَآ إِبۡرَٰهِيمَ بِٱلۡبُشۡرَىٰ قَالُواْ سَلَٰمٗاۖ قَالَ سَلَٰمٞۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَآءَ بِعِجۡلٍ حَنِيذٖ
69. መልዕክተኞቻችንም ወደ ኢብራሂም በልጅ መውለድ ብስራት መጡለትና ሰላም አሉት:: እሱም ሰላም አላቸው:: ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ::
阿拉伯语经注:
فَلَمَّا رَءَآ أَيۡدِيَهُمۡ لَا تَصِلُ إِلَيۡهِ نَكِرَهُمۡ وَأَوۡجَسَ مِنۡهُمۡ خِيفَةٗۚ قَالُواْ لَا تَخَفۡ إِنَّآ أُرۡسِلۡنَآ إِلَىٰ قَوۡمِ لُوطٖ
70. እጆቻቸዉም ወደ ምግቡ የማይደርሱ መሆናቸውን ባየ ጊዜ ተግባራቸው እንግዳ ሆነበት:: ከእነርሱም ፍርሃት ተሰማው:: «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ህዝቦች ተልከናልና።» አሉት።
阿拉伯语经注:
وَٱمۡرَأَتُهُۥ قَآئِمَةٞ فَضَحِكَتۡ فَبَشَّرۡنَٰهَا بِإِسۡحَٰقَ وَمِن وَرَآءِ إِسۡحَٰقَ يَعۡقُوبَ
71. ሚስቱም ቁማ ነበርና ሳቀች:: እናም በኢስሓቅ አበሰርናት:: ከኢስሐቅም በኋላ በልጁ በየዕቁብ አበሰርናት::
阿拉伯语经注:
قَالَتۡ يَٰوَيۡلَتَىٰٓ ءَأَلِدُ وَأَنَا۠ عَجُوزٞ وَهَٰذَا بَعۡلِي شَيۡخًاۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَيۡءٌ عَجِيبٞ
72. እርሷም «ዋልኝ እኔ አሮጊት ይህም ባለቤቴ ሽማግሌ ሆኖ ሳለ እወልዳለሁን? ይህ በእርግጥ አስደናቂ ነገር ነው።» አለች።
阿拉伯语经注:
قَالُوٓاْ أَتَعۡجَبِينَ مِنۡ أَمۡرِ ٱللَّهِۖ رَحۡمَتُ ٱللَّهِ وَبَرَكَٰتُهُۥ عَلَيۡكُمۡ أَهۡلَ ٱلۡبَيۡتِۚ إِنَّهُۥ حَمِيدٞ مَّجِيدٞ
73. «በአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን? :: የአላህ እዝነትና በረከት በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን:: እሱ ምስጉንና ለጋሽ ነውና።» አሉ።
阿拉伯语经注:
فَلَمَّا ذَهَبَ عَنۡ إِبۡرَٰهِيمَ ٱلرَّوۡعُ وَجَآءَتۡهُ ٱلۡبُشۡرَىٰ يُجَٰدِلُنَا فِي قَوۡمِ لُوطٍ
74. ከኢብራሂም ፍራቻው በሄደለትና ብስራት በመጣችለት ጊዜ በሉጥ ህዝቦች ነገር ይከራከረን ጀመር::
阿拉伯语经注:
إِنَّ إِبۡرَٰهِيمَ لَحَلِيمٌ أَوَّٰهٞ مُّنِيبٞ
75. ኢብራሂም በእርግጥ ታጋሽ፤ አልቃሻ (እጅግ የሚማፀን) እና መላሳ ነውና::
阿拉伯语经注:
يَٰٓإِبۡرَٰهِيمُ أَعۡرِضۡ عَنۡ هَٰذَآۖ إِنَّهُۥ قَدۡ جَآءَ أَمۡرُ رَبِّكَۖ وَإِنَّهُمۡ ءَاتِيهِمۡ عَذَابٌ غَيۡرُ مَرۡدُودٖ
76. (እነርሱም አሉት): «ኢብራሂም ሆይ! ይህን ክርክር ተው:: እነሆ የጌታህ ትዕዛዝ በእርግጥ መጥቷል:: እነርሱም የማይመለስ ቅጣት የሚመጣባቸው ናቸው።»
阿拉伯语经注:
وَلَمَّا جَآءَتۡ رُسُلُنَا لُوطٗا سِيٓءَ بِهِمۡ وَضَاقَ بِهِمۡ ذَرۡعٗا وَقَالَ هَٰذَا يَوۡمٌ عَصِيبٞ
77. መልዕክተኞቻችንም ወደ ሉጥ በመጡ ጊዜ በእነርሱ ምክንያት አዘነ:: ልቡም በእነርሱ ተጨነቀ:: «ይህ ብርቱ ቀን ነዉ።» አለም።
阿拉伯语经注:
وَجَآءَهُۥ قَوۡمُهُۥ يُهۡرَعُونَ إِلَيۡهِ وَمِن قَبۡلُ كَانُواْ يَعۡمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ هَٰٓؤُلَآءِ بَنَاتِي هُنَّ أَطۡهَرُ لَكُمۡۖ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَلَا تُخۡزُونِ فِي ضَيۡفِيٓۖ أَلَيۡسَ مِنكُمۡ رَجُلٞ رَّشِيدٞ
78. ህዝቦቹም ወደ እርሱ እየተጣደፉ መጡና ከዚህም በፊት መጥፎ ሥራዎችን ይሠሩ ነበር:: «ህዝቦቼ ሆይ! እነዚህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው:: ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ ናቸው:: አግቧቸው እናም አላህን ፍሩ:: በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ። ከናንተ ውስጥ አንድ ቅን ሰው እንኳን የለምን?» አላቸው::
阿拉伯语经注:
قَالُواْ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَا لَنَا فِي بَنَاتِكَ مِنۡ حَقّٖ وَإِنَّكَ لَتَعۡلَمُ مَا نُرِيدُ
79. «ከሴቶች ልጆችህ እኛ ምንም ጉዳይ የሌለን መሆኑን በትክክል ታውቃለህ:: አንተም የምንሻውን በእርግጥ ታውቃለህ።» አሉት።
阿拉伯语经注:
قَالَ لَوۡ أَنَّ لِي بِكُمۡ قُوَّةً أَوۡ ءَاوِيٓ إِلَىٰ رُكۡنٖ شَدِيدٖ
80. «በእናንተ ላይ ኃይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ብጠጋ ኖሮ (የምሠራውን በሠራሁ ነበር)።» አላቸው።
阿拉伯语经注:
قَالُواْ يَٰلُوطُ إِنَّا رُسُلُ رَبِّكَ لَن يَصِلُوٓاْ إِلَيۡكَۖ فَأَسۡرِ بِأَهۡلِكَ بِقِطۡعٖ مِّنَ ٱلَّيۡلِ وَلَا يَلۡتَفِتۡ مِنكُمۡ أَحَدٌ إِلَّا ٱمۡرَأَتَكَۖ إِنَّهُۥ مُصِيبُهَا مَآ أَصَابَهُمۡۚ إِنَّ مَوۡعِدَهُمُ ٱلصُّبۡحُۚ أَلَيۡسَ ٱلصُّبۡحُ بِقَرِيبٖ
81. «ሉጥ ሆይ! እኛ የጌታህ መልዕክተኞች ነን:: ህዝቦች ወደ አንተ በክፉ አይደርሱብህም:: ቤተሰብህንም ይዘህ ከሌሊቱ በከፊሉ ውስጥ ሂድ:: ከናንተም አንድም ወደ ኋላው አይገላመጥ:: ሚስትህ ብቻ ስትቀር:: እነሆ እርሷንማ እነርሱን የሚያገኛቸው ስቃይ ሁሉ ያገኛታልና:: ቀጠሯቸው ንጋቱ ላይ ነው:: ንጋቱ ቅርብ አይደለምን?» አሉት።
阿拉伯语经注:
فَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا جَعَلۡنَا عَٰلِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهَا حِجَارَةٗ مِّن سِجِّيلٖ مَّنضُودٖ
82. እናም ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ከተማይቱን ላይዋን ከታችዋ አድርገን ገለበጥናት:: ተከታታይም የሆነን የሸክላ ድንጋይ በእርሷ ላይ አዘነብንባት::
阿拉伯语经注:
مُّسَوَّمَةً عِندَ رَبِّكَۖ وَمَا هِيَ مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ بِبَعِيدٖ
83. ከጌታህ ዘንድ ምልክት የተደረገባት ስትሆን (አዘነብናት)። እርሷም (መንደሯ) ከበደለኞቹ ህዝቦች ሩቅ አይደለችም::
阿拉伯语经注:
۞ وَإِلَىٰ مَدۡيَنَ أَخَاهُمۡ شُعَيۡبٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥۖ وَلَا تَنقُصُواْ ٱلۡمِكۡيَالَ وَٱلۡمِيزَانَۖ إِنِّيٓ أَرَىٰكُم بِخَيۡرٖ وَإِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٖ مُّحِيطٖ
84. ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን:: አላቸውም: «ህዝቦቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ:: ከእሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም:: ስፍርንና ሚዛንን አታጉሉ:: እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ:: እኔም በእናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ::
阿拉伯语经注:
وَيَٰقَوۡمِ أَوۡفُواْ ٱلۡمِكۡيَالَ وَٱلۡمِيزَانَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا تَبۡخَسُواْ ٱلنَّاسَ أَشۡيَآءَهُمۡ وَلَا تَعۡثَوۡاْ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُفۡسِدِينَ
85. «ህዝቦቼ ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ:: ሰዎችን መብቶቻቸውን አታጓድሉባቸው:: በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ።
阿拉伯语经注:
بَقِيَّتُ ٱللَّهِ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَۚ وَمَآ أَنَا۠ عَلَيۡكُم بِحَفِيظٖ
86. «አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው:: ትክክለኛ አማኞች እንደ ሆናችሁ አላህ በሰጣችሁ ውደዱ። እኔም መካሪ እንጂ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም።»
阿拉伯语经注:
قَالُواْ يَٰشُعَيۡبُ أَصَلَوٰتُكَ تَأۡمُرُكَ أَن نَّتۡرُكَ مَا يَعۡبُدُ ءَابَآؤُنَآ أَوۡ أَن نَّفۡعَلَ فِيٓ أَمۡوَٰلِنَا مَا نَشَٰٓؤُاْۖ إِنَّكَ لَأَنتَ ٱلۡحَلِيمُ ٱلرَّشِيدُ
87. «ሹዐይብ ሆይ! ስግደትህ አባቶቻችን የሚገዙትን ጣኦታት እንድንተው ወይም በገንዘቦቻችን የምንሻውን መሥራትን እንድንተው ታዝሃለችን? አንተ በእርግጥ ታጋሹ ቅኑው አንተ ነህና።» አሉት።
阿拉伯语经注:
قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كُنتُ عَلَىٰ بَيِّنَةٖ مِّن رَّبِّي وَرَزَقَنِي مِنۡهُ رِزۡقًا حَسَنٗاۚ وَمَآ أُرِيدُ أَنۡ أُخَالِفَكُمۡ إِلَىٰ مَآ أَنۡهَىٰكُمۡ عَنۡهُۚ إِنۡ أُرِيدُ إِلَّا ٱلۡإِصۡلَٰحَ مَا ٱسۡتَطَعۡتُۚ وَمَا تَوۡفِيقِيٓ إِلَّا بِٱللَّهِۚ عَلَيۡهِ تَوَكَّلۡتُ وَإِلَيۡهِ أُنِيبُ
88. (እርሱም) አለ: «ህዝቦቼ ሆይ! ንገሩኝ እስቲ ከጌታዬ በሆነ አስረጅ ላይ ሆኜ ከእርሱም የሆነን መልካም ሲሳይ ቢሰጠኝ በቅጥፈት ልቀላቅለው ይገባልን? የከለከልኳችሁንም ነገር በመፈጸም ልለያችሁ አልሻም:: በተቻለኝ ያህል ማበጀትን እንጂ አልሻም:: ለደግ ሥራ መታደሌ በአላህ ፈቃድ ብቻ እንጂ በሌላ አይደለም:: በእርሱ ላይ ብቻ ተመካሁ:: ወደ እርሱም እመለሳለሁ።
阿拉伯语经注:
وَيَٰقَوۡمِ لَا يَجۡرِمَنَّكُمۡ شِقَاقِيٓ أَن يُصِيبَكُم مِّثۡلُ مَآ أَصَابَ قَوۡمَ نُوحٍ أَوۡ قَوۡمَ هُودٍ أَوۡ قَوۡمَ صَٰلِحٖۚ وَمَا قَوۡمُ لُوطٖ مِّنكُم بِبَعِيدٖ
89. «ወገኖቼ ሆይ! እኔን መከራከራችሁ የኑህን ህዝቦች ወይም የሁድን ህዝቦች ወይም የሷሊህን ህዝቦች ያገኛቸው ቅጣት ብጤ አይነት እንዲያገኛችሁ አይገፋፋችሁ:: የሉጥም ህዝቦች ከናንተ ሩቅ አይደሉም።
阿拉伯语经注:
وَٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ ثُمَّ تُوبُوٓاْ إِلَيۡهِۚ إِنَّ رَبِّي رَحِيمٞ وَدُودٞ
90. «ጌታችሁንም ምህረት ለምኑት ከዚያ ወደ እርሱ ተመለሱ። ጌታዬ አዛኝና ወዳድ ነውና።» አለ።
阿拉伯语经注:
قَالُواْ يَٰشُعَيۡبُ مَا نَفۡقَهُ كَثِيرٗا مِّمَّا تَقُولُ وَإِنَّا لَنَرَىٰكَ فِينَا ضَعِيفٗاۖ وَلَوۡلَا رَهۡطُكَ لَرَجَمۡنَٰكَۖ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡنَا بِعَزِيزٖ
91. «ሹዐይብ ሆይ! ከምትለው ነገር ብዙውን አናውቀዉም (አይገባንም):: እኛም አንተን በኛ ውስጥ ደከማ ሆነህ እናይሃለን:: ጎሶችህም ባልኖሩ ኖሮ በወገርንህ ነበር:: አንተም በእኛ ላይ የተከበርክ አይደለህም።» አሉት::
阿拉伯语经注:
قَالَ يَٰقَوۡمِ أَرَهۡطِيٓ أَعَزُّ عَلَيۡكُم مِّنَ ٱللَّهِ وَٱتَّخَذۡتُمُوهُ وَرَآءَكُمۡ ظِهۡرِيًّاۖ إِنَّ رَبِّي بِمَا تَعۡمَلُونَ مُحِيطٞ
92. (እርሱም) አለ: «ህዝቦቼ ሆይ? ጎሳዎቼ በእናንተ ላይ ከአላህ ይልቅ የከበሩ ናቸውን? አላህን ከኋላችሁ ወደ ጀርባ አደረጋችሁት:: ጌታዬ በምትሠሩት ሁሉ ከባቢ ነው።
阿拉伯语经注:
وَيَٰقَوۡمِ ٱعۡمَلُواْ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمۡ إِنِّي عَٰمِلٞۖ سَوۡفَ تَعۡلَمُونَ مَن يَأۡتِيهِ عَذَابٞ يُخۡزِيهِ وَمَنۡ هُوَ كَٰذِبٞۖ وَٱرۡتَقِبُوٓاْ إِنِّي مَعَكُمۡ رَقِيبٞ
93. «ህዝቦቼ ሆይ! በችሎታችሁ ልክ ሥሩ እኔ ሠሪ ነኝ። የሚያዋርደው ቅጣት የሚመጣበትንና እርሱ ውሸታም የሆነው ማን እንደ ሆነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ:: ጠብቁም እኔም ከናንተ ጋር ተጠባባቂ ነኝና።» አለ።
阿拉伯语经注:
وَلَمَّا جَآءَ أَمۡرُنَا نَجَّيۡنَا شُعَيۡبٗا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ بِرَحۡمَةٖ مِّنَّا وَأَخَذَتِ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ ٱلصَّيۡحَةُ فَأَصۡبَحُواْ فِي دِيَٰرِهِمۡ جَٰثِمِينَ
94. ትዕዛዛችን በመጣ ጊዜ ሹዐይብንና እነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው ችሮታ አዳን:: እነዚያን የበደሉትንም (የጂብሪል) ጩኸት ያዘቻቸው። በየቤቶቻቸዉም ውስጥ ተንከፍርረው አደሩ::
阿拉伯语经注:
كَأَن لَّمۡ يَغۡنَوۡاْ فِيهَآۗ أَلَا بُعۡدٗا لِّمَدۡيَنَ كَمَا بَعِدَتۡ ثَمُودُ
95. በእርሷ ውስጥ እንዳልነበሩ ሆኑ:: አስተዉሉ! ሠሙድ ከአላህ እዝነት እንደራቀች መድየንም ትራቅ::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٍ
96. ሙሳንም በታዐምራቶቻችንና በግልጽ ብርሃን በእርግጥ ላክነው::
阿拉伯语经注:
إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَٱتَّبَعُوٓاْ أَمۡرَ فِرۡعَوۡنَۖ وَمَآ أَمۡرُ فِرۡعَوۡنَ بِرَشِيدٖ
ወደ ፈርዖንና ወደስዎቹ ላክነው፡፡የፈርዖንን ነገር ህዝቦቹ ተከተሉ፡፡ የፈርዖን ነገር ቀጥተኛ አል ነበረም፡፡
阿拉伯语经注:
يَقۡدُمُ قَوۡمَهُۥ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فَأَوۡرَدَهُمُ ٱلنَّارَۖ وَبِئۡسَ ٱلۡوِرۡدُ ٱلۡمَوۡرُودُ
በትንሳኤ ቀን ህዝቦቹን ይቀድማል፡፡ ከዚያም ወደ አሳት ያወርዳቸዋል፡፡ የሚገቡትም አገባብ ምንኛ ከፋ፡፡
阿拉伯语经注:
وَأُتۡبِعُواْ فِي هَٰذِهِۦ لَعۡنَةٗ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ بِئۡسَ ٱلرِّفۡدُ ٱلۡمَرۡفُودُ
99. በዚችም በቅርቢቱ ዓለም እርግማንን አስከተልናቸው:: በትንሳኤም ቀን እንደዚሁ። የተሰጡት ስጦታ ምንኛ ከፋ!
阿拉伯语经注:
ذَٰلِكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ ٱلۡقُرَىٰ نَقُصُّهُۥ عَلَيۡكَۖ مِنۡهَا قَآئِمٞ وَحَصِيدٞ
100. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ከላይ የተነገረው ከከተሞቹ ወሬዎች የተወሰነው ነው:: ባንተ ላይ እንተርከዋለን:: ከእርሷ ቋሚና እጭድም የሆነ አለ::
阿拉伯语经注:
وَمَا ظَلَمۡنَٰهُمۡ وَلَٰكِن ظَلَمُوٓاْ أَنفُسَهُمۡۖ فَمَآ أَغۡنَتۡ عَنۡهُمۡ ءَالِهَتُهُمُ ٱلَّتِي يَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مِن شَيۡءٖ لَّمَّا جَآءَ أَمۡرُ رَبِّكَۖ وَمَا زَادُوهُمۡ غَيۡرَ تَتۡبِيبٖ
101. እኛም አልበደልናቸዉም:: ግን ነፍሶቻቸውን በደሉ:: የጌታህ ጉዳይ በመጣ ጊዜ እነዚያ ከአላህ ሌላ የሚገዟቸው አማልክቶቻቸው ሁሉ በምንም አላዳኗቸዉም:: ከማክሰርም በስተቀር ምንም አልጨመሩላቸዉም::
阿拉伯语经注:
وَكَذَٰلِكَ أَخۡذُ رَبِّكَ إِذَآ أَخَذَ ٱلۡقُرَىٰ وَهِيَ ظَٰلِمَةٌۚ إِنَّ أَخۡذَهُۥٓ أَلِيمٞ شَدِيدٌ
102. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ ቅጣት የከተሞችን ሰዎች በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ ልክ እንደዚህ ነው:: ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚና ብርቱ ነው::
阿拉伯语经注:
إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لِّمَنۡ خَافَ عَذَابَ ٱلۡأٓخِرَةِۚ ذَٰلِكَ يَوۡمٞ مَّجۡمُوعٞ لَّهُ ٱلنَّاسُ وَذَٰلِكَ يَوۡمٞ مَّشۡهُودٞ
103. በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ:: ይህ የትንሳኤ ቀን ሰዎች በእርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው:: ይህ የሚጣዱት ቀን ነው::
阿拉伯语经注:
وَمَا نُؤَخِّرُهُۥٓ إِلَّا لِأَجَلٖ مَّعۡدُودٖ
104. ይህንን ቀን ለተቆጠረም (ለተወሰነ) ጊዜ እንጂ አናቆየዉም::
阿拉伯语经注:
يَوۡمَ يَأۡتِ لَا تَكَلَّمُ نَفۡسٌ إِلَّا بِإِذۡنِهِۦۚ فَمِنۡهُمۡ شَقِيّٞ وَسَعِيدٞ
105. በሚመጣ ቀን ማንኛዉም ነፍስ በእርሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትናገርም:: ከእነርሱም መናጢም (እድለቢስ) እድለኛም አለ::
阿拉伯语经注:
فَأَمَّا ٱلَّذِينَ شَقُواْ فَفِي ٱلنَّارِ لَهُمۡ فِيهَا زَفِيرٞ وَشَهِيقٌ
106. እነዚያ ያመጹትማ በእሳት ውስጥ ናቸው:: ለእነርሱ በእርሷ ውስጥ ማናፋትና መንሰቅሰቅ አላቸው::
阿拉伯语经注:
خَٰلِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ إِلَّا مَا شَآءَ رَبُّكَۚ إِنَّ رَبَّكَ فَعَّالٞ لِّمَا يُرِيدُ
107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ከፈለገው በስተቀር ሰማያትና ምድር እስከዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ በእሳት ውስጥ ይኖራሉ:: ጌታህ የሚፈልገውን ሠሪ ነውና::
阿拉伯语经注:
۞ وَأَمَّا ٱلَّذِينَ سُعِدُواْ فَفِي ٱلۡجَنَّةِ خَٰلِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ إِلَّا مَا شَآءَ رَبُّكَۖ عَطَآءً غَيۡرَ مَجۡذُوذٖ
108. እነዚያ እድለኞቹማ ጌታ ከሻው በስተቀር ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ሆነው በገነት ውስጥ ይኖራሉ:: የማያቋርጥ ስጦታን ተሰጡ::
阿拉伯语经注:
فَلَا تَكُ فِي مِرۡيَةٖ مِّمَّا يَعۡبُدُ هَٰٓؤُلَآءِۚ مَا يَعۡبُدُونَ إِلَّا كَمَا يَعۡبُدُ ءَابَآؤُهُم مِّن قَبۡلُۚ وَإِنَّا لَمُوَفُّوهُمۡ نَصِيبَهُمۡ غَيۡرَ مَنقُوصٖ
109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ከሓዲያን ከሚገዙት ጣኦት በመጠራጠር ውስጥ አትሁን:: አባቶቻቸው ከዚህ በፊት እንደሚገዙት እንጂ አይገዙም:: እኛም እነዚህን ፈንታቸውን የማይጓደል ሲሆን የምንሞላላቸው ነን::
阿拉伯语经注:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ فَٱخۡتُلِفَ فِيهِۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡۚ وَإِنَّهُمۡ لَفِي شَكّٖ مِّنۡهُ مُرِيبٖ
110. ለሙሳም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: በእርሱም ተለያዩበት። ከጌታህ ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው አሁን ይፈረድ ነበር:: እነርሱም ከእርሱ ከቁርኣን አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ናቸው::
阿拉伯语经注:
وَإِنَّ كُلّٗا لَّمَّا لَيُوَفِّيَنَّهُمۡ رَبُّكَ أَعۡمَٰلَهُمۡۚ إِنَّهُۥ بِمَا يَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ
111. ሁሉንም ጌታህ ሥራዎቻቸውን ምንዳቸውን በእርግጥ ይሞላላቸዋል:: እርሱ በሚሠሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::
阿拉伯语经注:
فَٱسۡتَقِمۡ كَمَآ أُمِرۡتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطۡغَوۡاْۚ إِنَّهُۥ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ
112. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደታዘዝከው ቀጥ በል። ካንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ። ወሰንንም አትለፉ። እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
阿拉伯语经注:
وَلَا تَرۡكَنُوٓاْ إِلَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ فَتَمَسَّكُمُ ٱلنَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِنۡ أَوۡلِيَآءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ
113. ወደ እነዚያም ወደ በደሉት ህዝቦች አትዘንበሉ:: እሳት ትነካችኋለችና:: ከአላህ ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም ከዚያ አትረዱም::
阿拉伯语经注:
وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ طَرَفَيِ ٱلنَّهَارِ وَزُلَفٗا مِّنَ ٱلَّيۡلِۚ إِنَّ ٱلۡحَسَنَٰتِ يُذۡهِبۡنَ ٱلسَّيِّـَٔاتِۚ ذَٰلِكَ ذِكۡرَىٰ لِلذَّٰكِرِينَ
114. ሶላትንም በቀን ጫፍና ጫፎች ከሌሊትም ክፍሎች ፈጽም:: መልካም ሥራዎች ኃጢአቶችን ያስወግዳሉና:: ይህ ለተገሳጮች ሁሉ ግሳጼ ነው::
阿拉伯语经注:
وَٱصۡبِرۡ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
115. ታገስ አላህ የበጎ ሠሪዎችን ምንዳ አያጠፋምና::
阿拉伯语经注:
فَلَوۡلَا كَانَ مِنَ ٱلۡقُرُونِ مِن قَبۡلِكُمۡ أُوْلُواْ بَقِيَّةٖ يَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلۡفَسَادِ فِي ٱلۡأَرۡضِ إِلَّا قَلِيلٗا مِّمَّنۡ أَنجَيۡنَا مِنۡهُمۡۗ وَٱتَّبَعَ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مَآ أُتۡرِفُواْ فِيهِ وَكَانُواْ مُجۡرِمِينَ
116. ከናንተ በፊት ከነበሩት ከክፍለ ዘመናት (ሰዎች) ውስጥ በምድር ላይ ከማበላሸት የሚከለክሉ የመልካም ሥራዎች ቅሪት ባለቤቶች ለምን አልነበሩም? ግን ከእነርሱ ያዳንናቸው ጥቂቶቹ ከለከሉና ዳኑ:: እነዚያም የበደሉት ሰዎች አልከለከሉም። በእርሱ የተቀማጠሉበትን ተድላ ተከተሉ አመጠኞችም ነበሩ::
阿拉伯语经注:
وَمَا كَانَ رَبُّكَ لِيُهۡلِكَ ٱلۡقُرَىٰ بِظُلۡمٖ وَأَهۡلُهَا مُصۡلِحُونَ
117. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ከተሞችን ባለቤቶቻቸው መልካም ሠሪዎች ሆነው ሳሉ በመበደል የሚያጠፋቸው አልነበረም::
阿拉伯语经注:
وَلَوۡ شَآءَ رَبُّكَ لَجَعَلَ ٱلنَّاسَ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗۖ وَلَا يَزَالُونَ مُخۡتَلِفِينَ
118. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በሻ ኖሮ ሰዎችን ሁሉ አንድ ህዝብ ባደረጋቸው ነበር። የተለያዩም ከመሆን አይወገዱም::
阿拉伯语经注:
إِلَّا مَن رَّحِمَ رَبُّكَۚ وَلِذَٰلِكَ خَلَقَهُمۡۗ وَتَمَّتۡ كَلِمَةُ رَبِّكَ لَأَمۡلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ ٱلۡجِنَّةِ وَٱلنَّاسِ أَجۡمَعِينَ
119. ጌታህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር ከመለያየት አይወገዱም:: ለዚሁም ነው የፈጠራቸው:: የጌታህ ቃልም «ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ።» በማለት ተፈጸመች::
阿拉伯语经注:
وَكُلّٗا نَّقُصُّ عَلَيۡكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَۚ وَجَآءَكَ فِي هَٰذِهِ ٱلۡحَقُّ وَمَوۡعِظَةٞ وَذِكۡرَىٰ لِلۡمُؤۡمِنِينَ
120. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞቹም ዜናዎች ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናጸናበትን እንተርክልሀለን። በዚህችም ሱራ እውነቱ ነገር፣ ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ መጥቶልሀል::
阿拉伯语经注:
وَقُل لِّلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ ٱعۡمَلُواْ عَلَىٰ مَكَانَتِكُمۡ إِنَّا عَٰمِلُونَ
121. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነዚያም ለማያምኑት (እንዲህ) በላቸው: «ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ሥሩ:: እኛ ሠሪዎች ነን።
阿拉伯语经注:
وَٱنتَظِرُوٓاْ إِنَّا مُنتَظِرُونَ
122. «የራሳችሁን ውጤት ተጠባበቁ እኛ ተጠባባቂዎች ነንና።» በላቸው::
阿拉伯语经注:
وَلِلَّهِ غَيۡبُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَإِلَيۡهِ يُرۡجَعُ ٱلۡأَمۡرُ كُلُّهُۥ فَٱعۡبُدۡهُ وَتَوَكَّلۡ عَلَيۡهِۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ
123. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰማያትና በምድር ያለው ሚስጥር ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: ሁሉም ነገር ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳል:: ስለዚህ እሱን ብቻ ተገዛው:: በእርሱም ላይ ብቻ ተመካ:: ጌታህም ከሚሰሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም::
阿拉伯语经注:
 
含义的翻译 章: 呼德
章节目录 页码
 
《古兰经》译解 - 阿姆哈拉语翻译 - 非洲学院。 - 译解目录

由穆罕默德·宰尼·扎赫尔丁翻译。由非洲学院出版。

关闭