Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची


अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-निसा   आयत:
أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ يَزۡعُمُونَ أَنَّهُمۡ ءَامَنُواْ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ وَمَآ أُنزِلَ مِن قَبۡلِكَ يُرِيدُونَ أَن يَتَحَاكَمُوٓاْ إِلَى ٱلطَّٰغُوتِ وَقَدۡ أُمِرُوٓاْ أَن يَكۡفُرُواْ بِهِۦۖ وَيُرِيدُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَن يُضِلَّهُمۡ ضَلَٰلَۢا بَعِيدٗا
60. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ «ባንተ ላይ በተወረደውና ካንተ በፊትም በተወረደው አምነናል።» ወደ ሚሉት አላየህምን? በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲሆኑ ወደ ጣኦት መፋረድን ይፈልጋሉ:: ሰይጣንም ከእውነት የራቀን መሳሳት ሊያሳስታቸው ይፈልጋል።
अरबी तफ़सीरें:
وَإِذَا قِيلَ لَهُمۡ تَعَالَوۡاْ إِلَىٰ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ وَإِلَى ٱلرَّسُولِ رَأَيۡتَ ٱلۡمُنَٰفِقِينَ يَصُدُّونَ عَنكَ صُدُودٗا
61. ለእነርሱም፡- «አላህ ወደ አወረደው ቁርኣንና ወደ መልዕክተኛው ኑ።» በተባሉ ጊዜ አስመሳዮችን ካንተ በሀይል ሲሸሹ ታያቸዋለህ።
अरबी तफ़सीरें:
فَكَيۡفَ إِذَآ أَصَٰبَتۡهُم مُّصِيبَةُۢ بِمَا قَدَّمَتۡ أَيۡدِيهِمۡ ثُمَّ جَآءُوكَ يَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ إِنۡ أَرَدۡنَآ إِلَّآ إِحۡسَٰنٗا وَتَوۡفِيقًا
62. እጆቻቸዉም ባስቀደሙት ጥፋት ምክንያት መከራ በደረሰባቸውና ከዚያ «ደግን ሀሳብና ማስማማትን እንጂ ሌላን አልፈለግንም።» በማለት በአላህ የሚምሉ ሆነው ወደ አንተ በመጡ ጊዜ እንዴት ይሆናል?
अरबी तफ़सीरें:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ يَعۡلَمُ ٱللَّهُ مَا فِي قُلُوبِهِمۡ فَأَعۡرِضۡ عَنۡهُمۡ وَعِظۡهُمۡ وَقُل لَّهُمۡ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ قَوۡلَۢا بَلِيغٗا
63. እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው:: ከእነርሱ ራስህን አግልል:: ገስፃቸዉም:: ለእነርሱም በነፍሶቻቸው ውስጥ ጠልቆ የሚገባ ጠንካራ ቃል ተናገራቸው።
अरबी तफ़सीरें:
وَمَآ أَرۡسَلۡنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا لِيُطَاعَ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ وَلَوۡ أَنَّهُمۡ إِذ ظَّلَمُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ جَآءُوكَ فَٱسۡتَغۡفَرُواْ ٱللَّهَ وَٱسۡتَغۡفَرَ لَهُمُ ٱلرَّسُولُ لَوَجَدُواْ ٱللَّهَ تَوَّابٗا رَّحِيمٗا
64. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ማንንም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጂ አልላክንም:: እነርሱም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ ወደ አንተ መጥተው አላህን ምህረት በለመኑና መልዕክተኛዉም ለእነርሱ ምህረትን በለመነላቸው ኖሮ አላህን ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ሆኖ ባገኙት ነበር።
अरबी तफ़सीरें:
فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤۡمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيۡنَهُمۡ ثُمَّ لَا يَجِدُواْ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ حَرَجٗا مِّمَّا قَضَيۡتَ وَيُسَلِّمُواْ تَسۡلِيمٗا
65. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጉዳዩ እነርሱ እንዳሉት አይደለም:: በጌታህ እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ የሚያስፈርዱህ ሆነው ከዚያ ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አማኝ አይሆኑም::
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-निसा
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी द्वारा प्रकाशित.

बंद करें