Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-निसा   आयत:
۞ إِنَّآ أَوۡحَيۡنَآ إِلَيۡكَ كَمَآ أَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ نُوحٖ وَٱلنَّبِيِّـۧنَ مِنۢ بَعۡدِهِۦۚ وَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡمَٰعِيلَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ وَٱلۡأَسۡبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَٰرُونَ وَسُلَيۡمَٰنَۚ وَءَاتَيۡنَا دَاوُۥدَ زَبُورٗا
163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወደ ኑህና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነብያት መልዕክታችንን እንዳወረድን ሁሉ ወደ አንተም ቁርኣንን አወረድን:: ወደ ነብዩ ኢብራሂም፤ ወደ ነብዩ ኢስማኢልም፤ ወደ ነብዩ ኢስሃቅም፤ ወደ ነብዩ የዕቆብም፤ ወደ ነገዶችም፤ ወደ ነብዩ ዒሳም፤ ወደ ነብዩ አዩብም፤ ወደ ነብዩ ዩኑስም፤ ወደ ነብዩ ሃሩንና ወደ ነብዩ ሱለይማን አወረድን:: ለነብዩ ዳውድም ዘቡርን ሰጠነው::
अरबी तफ़सीरें:
وَرُسُلٗا قَدۡ قَصَصۡنَٰهُمۡ عَلَيۡكَ مِن قَبۡلُ وَرُسُلٗا لَّمۡ نَقۡصُصۡهُمۡ عَلَيۡكَۚ وَكَلَّمَ ٱللَّهُ مُوسَىٰ تَكۡلِيمٗا
164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚህም በፊት በአንተ ላይ በእርግጥ የተረክናቸውን መልዕክተኞች ባንተ ላይም ያልተረክናቸውንም መልዕክተኞች እንደላክን ሁሉ አንተን ላክንህ:: አላህ ነብዩ ሙሳንም ማነጋገርን አነጋገረው::
अरबी तफ़सीरें:
رُّسُلٗا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى ٱللَّهِ حُجَّةُۢ بَعۡدَ ٱلرُّسُلِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمٗا
165. ከመልዕክተኞች በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ ምንም አስረጂ እንዳይኖራቸው አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርገን መልዕክተኞችን ላክን:: አላህ ሁሉን አሸናፊ፤ ጥበበኛ ነውና::
अरबी तफ़सीरें:
لَّٰكِنِ ٱللَّهُ يَشۡهَدُ بِمَآ أَنزَلَ إِلَيۡكَۖ أَنزَلَهُۥ بِعِلۡمِهِۦۖ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَشۡهَدُونَۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدًا
166. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ግን ባንተ ላይ ባወረደው ቁርኣን ይመሰክራል:: በእውቀቱ አወረደው:: መላዕክቱም ይመሰክራሉ:: መስካሪነትም በአላህ ብቻ በቃ::
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ قَدۡ ضَلُّواْ ضَلَٰلَۢا بَعِيدًا
167. እነዚያ በአላህ የካዱና ከአላህ መንገድም ሰዎችን ያገዱ ሰዎች ከእውነት የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳቱ::
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَظَلَمُواْ لَمۡ يَكُنِ ٱللَّهُ لِيَغۡفِرَ لَهُمۡ وَلَا لِيَهۡدِيَهُمۡ طَرِيقًا
168. እነዚያ የካዱና የበደሉ አላህ የሚምራቸውና ቅን መንገድን የሚመራቸው አይደለም::
अरबी तफ़सीरें:
إِلَّا طَرِيقَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٗا
169. ግን በውስጧ ለዘልዓለም ዘወታሪዎች ሲሆኑ የገሀነምን መንገድ ይመራቸዋል:: ይህም በአላህ ላይ ገር ነው::
अरबी तफ़सीरें:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدۡ جَآءَكُمُ ٱلرَّسُولُ بِٱلۡحَقِّ مِن رَّبِّكُمۡ فَـَٔامِنُواْ خَيۡرٗا لَّكُمۡۚ وَإِن تَكۡفُرُواْ فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا
170. እናንተ ሰዎች ሆይ! መልዕክተኛው እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ:: እናም ባመጣው እመኑ ለእናንተ የተሻለ ይሆናል:: በአላህ ብትክዱም እሱን (ቅንጣት) አትጎዱትም:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-निसा
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी की ओर से निर्गत.

बंद करें