Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-निसा   आयत:
وَٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمۡوَٰلَهُمۡ رِئَآءَ ٱلنَّاسِ وَلَا يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَلَا بِٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۗ وَمَن يَكُنِ ٱلشَّيۡطَٰنُ لَهُۥ قَرِينٗا فَسَآءَ قَرِينٗا
38. እነዚያ ለሰዎች ይዩልን ሲሉ ገንዘቦቻቸውን የሚሰጡ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የማያምኑ ይቀጣሉ:: ሰይጣንም የእሱ ጓደኛው የሆነለት ሁሉ ጓደኛነቱ ከፋ!
अरबी तफ़सीरें:
وَمَاذَا عَلَيۡهِمۡ لَوۡ ءَامَنُواْ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِ وَأَنفَقُواْ مِمَّا رَزَقَهُمُ ٱللَّهُۚ وَكَانَ ٱللَّهُ بِهِمۡ عَلِيمًا
39. በአላህና በመጨረሻው ቀን ባመኑና አላህ ከሰጣቸዉም ሲሳይ በለገሱ ኖሮ በእነርሱ ላይ ምን ጉዳት ነበረ? አላህ በእነርሱ ሁኔታ አዋቂ ነውና::
अरबी तफ़सीरें:
إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَظۡلِمُ مِثۡقَالَ ذَرَّةٖۖ وَإِن تَكُ حَسَنَةٗ يُضَٰعِفۡهَا وَيُؤۡتِ مِن لَّدُنۡهُ أَجۡرًا عَظِيمٗا
40. አላህ የብናኝን ክብደት ያህል እንኳን አይበድልም:: መልካም ስራ ብትሆንም ይደራርባታል:: ከእርሱም ዘንድ ታላቅን ምንዳ ይሰጣል::
अरबी तफ़सीरें:
فَكَيۡفَ إِذَا جِئۡنَا مِن كُلِّ أُمَّةِۭ بِشَهِيدٖ وَجِئۡنَا بِكَ عَلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِ شَهِيدٗا
41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሕዝቦች ሁሉ መስካሪን ባመጣንና አንተንም በእነዚህ (ባንተ ህዝቦች) ላይ መስካሪ አድርገን በምናመጣህ ጊዜ የከሓዲያን ሁኔታ እንዴት ይሆን?
अरबी तफ़सीरें:
يَوۡمَئِذٖ يَوَدُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَعَصَوُاْ ٱلرَّسُولَ لَوۡ تُسَوَّىٰ بِهِمُ ٱلۡأَرۡضُ وَلَا يَكۡتُمُونَ ٱللَّهَ حَدِيثٗا
42. በዚያ ቀን እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችና መልዕክተኛውን ያልታዘዙት ምድር በእነርሱ ላይ ብትደፋባቸው ይመኛሉ:: ከአላህም ወሬን አይደብቁም።
अरबी तफ़सीरें:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَقۡرَبُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَنتُمۡ سُكَٰرَىٰ حَتَّىٰ تَعۡلَمُواْ مَا تَقُولُونَ وَلَا جُنُبًا إِلَّا عَابِرِي سَبِيلٍ حَتَّىٰ تَغۡتَسِلُواْۚ وَإِن كُنتُم مَّرۡضَىٰٓ أَوۡ عَلَىٰ سَفَرٍ أَوۡ جَآءَ أَحَدٞ مِّنكُم مِّنَ ٱلۡغَآئِطِ أَوۡ لَٰمَسۡتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَلَمۡ تَجِدُواْ مَآءٗ فَتَيَمَّمُواْ صَعِيدٗا طَيِّبٗا فَٱمۡسَحُواْ بِوُجُوهِكُمۡ وَأَيۡدِيكُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَفُوًّا غَفُورًا
43. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የምትሉትን ነገር ለይታችሁ አስከምታውቁ ድረስ የሰከራችሁ ሆናችሁ ወደ ሶላት አትቅረቡ:: ጀናባ ስትሆኑም መንገድን አላፊዎች ካልሆናችሁ በስተቀር ሙሉ አካላታችሁን እስከምትታጥቡ ድረስ መስጊድን አትቅረቡ:: በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትሆኑ ወይም ከናንተ አንዱ ከአይነ ምድር ቢጸዳዳ ወይም ከሴቶች ጋር ብትነካኩና ( የግብረስጋ ግንኙነት ብትፈጽሙና) ውሃን ባታገኙ ንጹህ የሆነን የምድር ገጽ (አፈርን) አብሱ:: ከዚያ ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን በእርሱ አብሱ:: አላህ ይቅር ባይና መሀሪ ነውና።
अरबी तफ़सीरें:
أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ أُوتُواْ نَصِيبٗا مِّنَ ٱلۡكِتَٰبِ يَشۡتَرُونَ ٱلضَّلَٰلَةَ وَيُرِيدُونَ أَن تَضِلُّواْ ٱلسَّبِيلَ
44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ የእውቀት ድርሻን ወደ ተሰጡት ክፍሎች አላየህም? ጥመትን በቅንነት ይገዛሉ:: መንገድንም እንድትሳሳቱ ይፈልጋሉ።
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-निसा
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी की ओर से निर्गत.

बंद करें