Check out the new design

क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी * - अनुवादों की सूची


अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-निसा   आयत:
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ سَنُدۡخِلُهُمۡ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۖ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٗاۚ وَمَنۡ أَصۡدَقُ مِنَ ٱللَّهِ قِيلٗا
122. እነዚያ በአላህ ያመኑትና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ እናስገባቸዋለን:: አላህ እውነተኛን ተስፋ ሰጣቸው:: በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማን ነው?
अरबी तफ़सीरें:
لَّيۡسَ بِأَمَانِيِّكُمۡ وَلَآ أَمَانِيِّ أَهۡلِ ٱلۡكِتَٰبِۗ مَن يَعۡمَلۡ سُوٓءٗا يُجۡزَ بِهِۦ وَلَا يَجِدۡ لَهُۥ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلِيّٗا وَلَا نَصِيرٗا
123. ነገሩ በምኞታችሁና በመጽሐፉ ሰዎች ምኞት አይደለም:: መጥፎን የሚሰራ ሁሉ በእርሱ ይመነዳል:: ለእርሱም ከአላህ ሌላ ጠባቂን ረዳትንም አያገኝም::
अरबी तफ़सीरें:
وَمَن يَعۡمَلۡ مِنَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ مِن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَأُوْلَٰٓئِكَ يَدۡخُلُونَ ٱلۡجَنَّةَ وَلَا يُظۡلَمُونَ نَقِيرٗا
124. ከወንድ ወይም ከሴት አማኝ ሆነው ከበጎ ስራዎች አንድንም ነገር የሚሰሩ ገነት ይገባሉ:: በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳን አይበደሉም።
अरबी तफ़सीरें:
وَمَنۡ أَحۡسَنُ دِينٗا مِّمَّنۡ أَسۡلَمَ وَجۡهَهُۥ لِلَّهِ وَهُوَ مُحۡسِنٞ وَٱتَّبَعَ مِلَّةَ إِبۡرَٰهِيمَ حَنِيفٗاۗ وَٱتَّخَذَ ٱللَّهُ إِبۡرَٰهِيمَ خَلِيلٗا
125. መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን አለ? አላህ ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጎ ያዘው::
अरबी तफ़सीरें:
وَلِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٖ مُّحِيطٗا
126. በሰማያትና በምድር ያለው ነገር ሁሉ የአላህ ነው:: አላህ በነገሩ ሁሉ በእውቀት ከባቢ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
وَيَسۡتَفۡتُونَكَ فِي ٱلنِّسَآءِۖ قُلِ ٱللَّهُ يُفۡتِيكُمۡ فِيهِنَّ وَمَا يُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فِي ٱلۡكِتَٰبِ فِي يَتَٰمَى ٱلنِّسَآءِ ٱلَّٰتِي لَا تُؤۡتُونَهُنَّ مَا كُتِبَ لَهُنَّ وَتَرۡغَبُونَ أَن تَنكِحُوهُنَّ وَٱلۡمُسۡتَضۡعَفِينَ مِنَ ٱلۡوِلۡدَٰنِ وَأَن تَقُومُواْ لِلۡيَتَٰمَىٰ بِٱلۡقِسۡطِۚ وَمَا تَفۡعَلُواْ مِنۡ خَيۡرٖ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِهِۦ عَلِيمٗا
127. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ) ስለ ሴቶች ጉዳይ ይጠይቁሃል። «አላህ ስለነሱ ይነግራችኋል:: ያም በመጽሐፍ ውስጥ በእናንተ ላይ የሚነበበው ሲሆን በእነዚያ ከውርስ የተደነገገላቸውን ድርሻ በማትሰጧቸው ሴቶችና ልታገቧቸው በማትፈልጉት የቲሞች ሴቶች ይህንን እንዳታደርጉ፤ ህፃናት ለሆኑትም ደካሞች መብታቸውን እንድትሰጡ፤ ለየቲሞች በትክክል እንድትቆሙ ይነገራችኋል።» በላቸው:: ከበጎም ስራ የሆነን ማንኛውንም ስራ ብትሰሩ አላህ እርሱን አዋቂ ነው::
अरबी तफ़सीरें:
 
अर्थों का अनुवाद सूरा: अन्-निसा
सूरों की सूची पृष्ठ संख्या
 
क़ुरआन के अर्थों का अनुवाद - अम्हारी अनुवाद - अफ्रीका अकादमी - अनुवादों की सूची

अनुवाद - मुहम्मद ज़ैन ज़हरुद्दीन. अफ्रीका अकादमी द्वारा प्रकाशित.

बंद करें