Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次


対訳 章: 婦人章   節:
وَٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِأَعۡدَآئِكُمۡۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَلِيّٗا وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ نَصِيرٗا
45. (ትክክለኛ አማኞች ሆይ!) አላህ ጠላቶቻችሁን ከናንተ በበለጠ አዋቂ ነው:: ጠባቂነትም በአላህ በቃ:: ረዳትነትም በአላህ በቃ።
アラビア語 クルアーン注釈:
مِّنَ ٱلَّذِينَ هَادُواْ يُحَرِّفُونَ ٱلۡكَلِمَ عَن مَّوَاضِعِهِۦ وَيَقُولُونَ سَمِعۡنَا وَعَصَيۡنَا وَٱسۡمَعۡ غَيۡرَ مُسۡمَعٖ وَرَٰعِنَا لَيَّۢا بِأَلۡسِنَتِهِمۡ وَطَعۡنٗا فِي ٱلدِّينِۚ وَلَوۡ أَنَّهُمۡ قَالُواْ سَمِعۡنَا وَأَطَعۡنَا وَٱسۡمَعۡ وَٱنظُرۡنَا لَكَانَ خَيۡرٗا لَّهُمۡ وَأَقۡوَمَ وَلَٰكِن لَّعَنَهُمُ ٱللَّهُ بِكُفۡرِهِمۡ فَلَا يُؤۡمِنُونَ إِلَّا قَلِيلٗا
46. ከእነዚያ ከአይሁዳውያን መካከል ንግግሮችን ከስፍራዎቹ የሚያጣምሙ አሉ። «ንግግርክን ሰማንና ትእዛዝክን አመጽን፤ የማትሰማም ስትሆን እስቲ ስማ።» ይላሉ:: በምላሶቻቸዉም ለማጣመምና ሃይማኖትንም ለመዝለፍ በማሰብ "ራዒና" ይላሉ:: እነርሱም «ሰማንና ታዘዝን፤ ስማን ተመልከተንም።» ባሉ ኖሮ ለእነርሱም መልካምና ትክክለኛ በሆነ ነበር:: ግን በክህደታቸው ምክንያት አላህ ረገማቸው:: ከእነርሱም መካከል ጥቂቶች እንጂ አያምኑም።
アラビア語 クルアーン注釈:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ ءَامِنُواْ بِمَا نَزَّلۡنَا مُصَدِّقٗا لِّمَا مَعَكُم مِّن قَبۡلِ أَن نَّطۡمِسَ وُجُوهٗا فَنَرُدَّهَا عَلَىٰٓ أَدۡبَارِهَآ أَوۡ نَلۡعَنَهُمۡ كَمَا لَعَنَّآ أَصۡحَٰبَ ٱلسَّبۡتِۚ وَكَانَ أَمۡرُ ٱللَّهِ مَفۡعُولًا
47. እናንተ መጽሐፉ የተሰጣችሁ ሰዎች ሆይ! ፊቶችን ሳናዞርና በጀርባዎች ላይ ሳንመልሳቸው ወይም የሠንበትን ባለቤቶች እንደረገምን ሳንረግማችሁ በፊት ከናንተ ጋር ያለውን የሚያረጋግጥ ሆኖ በአወረድነው ቁርኣን እመኑ:: የአላህም ትዕዛዝ ተፈፃሚ ነው።
アラビア語 クルアーン注釈:
إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَغۡفِرُ أَن يُشۡرَكَ بِهِۦ وَيَغۡفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَآءُۚ وَمَن يُشۡرِكۡ بِٱللَّهِ فَقَدِ ٱفۡتَرَىٰٓ إِثۡمًا عَظِيمًا
48. አላህ በእርሱ ማጋራትን ፈጽሞ አይምርም:: ከዚህ በታች (ውጭ) ያለውን ኃጢአት ግን ለሚሻው ሁሉ ይምራል:: በአላህ የሚያጋራ ሁሉ ታላቅን ኃጢአት በእርግጥ ቀጠፈ::
アラビア語 クルアーン注釈:
أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ يُزَكُّونَ أَنفُسَهُمۚ بَلِ ٱللَّهُ يُزَكِّي مَن يَشَآءُ وَلَا يُظۡلَمُونَ فَتِيلًا
49. ወደ እነዚያ ነፍሶቻቸውን ወደ ሚያጠሩት (ሚያወድሱት) አላየህምን? ይልቁንም አላህ ነው የሚፈልገውን የሚያጠራው። በተምር ፍሬ ስንጥቅ ላይ ያለችን ክር መሳይ ያህልም ቢሆን አይበደሉም።
アラビア語 クルアーン注釈:
ٱنظُرۡ كَيۡفَ يَفۡتَرُونَ عَلَى ٱللَّهِ ٱلۡكَذِبَۖ وَكَفَىٰ بِهِۦٓ إِثۡمٗا مُّبِينًا
50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ ላይ ውሸትን እንዴት እንደሚቀጥፉ ተመልከት። ግልጽ ወንጀል በርሱ በቃ።
アラビア語 クルアーン注釈:
أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ أُوتُواْ نَصِيبٗا مِّنَ ٱلۡكِتَٰبِ يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡجِبۡتِ وَٱلطَّٰغُوتِ وَيَقُولُونَ لِلَّذِينَ كَفَرُواْ هَٰٓؤُلَآءِ أَهۡدَىٰ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ سَبِيلًا
51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፉ ድርሻን ወደ ተሰጡት አላየህምን? በድግምትና በጣዖት ያምናሉ። ለእነዚያ በአላህ ለካዱትም እነርሱ በሃይማኖት ከእነዚያ በሙሐመድ ካመኑት ይበልጥ ቀና እንደሆኑ ይናገራሉ።
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 婦人章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる