Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次


対訳 章: 婦人章   節:
لِّلرِّجَالِ نَصِيبٞ مِّمَّا تَرَكَ ٱلۡوَٰلِدَانِ وَٱلۡأَقۡرَبُونَ وَلِلنِّسَآءِ نَصِيبٞ مِّمَّا تَرَكَ ٱلۡوَٰلِدَانِ وَٱلۡأَقۡرَبُونَ مِمَّا قَلَّ مِنۡهُ أَوۡ كَثُرَۚ نَصِيبٗا مَّفۡرُوضٗا
7. ለወንዶች ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ሲሞቱ ከተውት (ጥሪት ገንዘብ የውርስ) ድርሻ አላቸው:: ለሴቶችም ወላጆችና የቅርብ ዘመዶች ከተውት ከእርሱ ይነስም ይብዛም (የውርስ) ድርሻ አላቸው:: ለሁሉም የተወሰነ ድርሻ ተደንግጓል::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَإِذَا حَضَرَ ٱلۡقِسۡمَةَ أُوْلُواْ ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينُ فَٱرۡزُقُوهُم مِّنۡهُ وَقُولُواْ لَهُمۡ قَوۡلٗا مَّعۡرُوفٗا
8. የውርስ ክፍፍልን (ወራሽ ያልሆኑ) የዝምድና ባለቤቶች፤ የቲሞችና ሚስኪኖች በተገኙበት ጊዜ ከእርሱ ለግሱላቸው:: መልካምንም ንግግር ተናገሯቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَلۡيَخۡشَ ٱلَّذِينَ لَوۡ تَرَكُواْ مِنۡ خَلۡفِهِمۡ ذُرِّيَّةٗ ضِعَٰفًا خَافُواْ عَلَيۡهِمۡ فَلۡيَتَّقُواْ ٱللَّهَ وَلۡيَقُولُواْ قَوۡلٗا سَدِيدًا
9.   እነዚያ ከኋላቸው ደካማ ዝርያዎችን ቢተው ኖሮ በእነርሱ ላይ ምን ይደርስባቸው ይሆን ብለው የሚሰጉ ሰዎች ሁሉ (በየቲሞችም ላይ) ይህንኑ ይፍሩ:: አላህንም ይፍሩ:: ትክክለኛንም ቃል ይናገሩ::
アラビア語 クルアーン注釈:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَأۡكُلُونَ أَمۡوَٰلَ ٱلۡيَتَٰمَىٰ ظُلۡمًا إِنَّمَا يَأۡكُلُونَ فِي بُطُونِهِمۡ نَارٗاۖ وَسَيَصۡلَوۡنَ سَعِيرٗا
10. እነዚያ የየቲሞችን ገንዘቦች በግፍ የሚበሉ ሁሉ በሆዶቻቸው ውስጥ የሚበሉት እሳትን ብቻ ነው:: የገሀንም እሳትንም በእርግጥ ይገባሉ::
アラビア語 クルアーン注釈:
يُوصِيكُمُ ٱللَّهُ فِيٓ أَوۡلَٰدِكُمۡۖ لِلذَّكَرِ مِثۡلُ حَظِّ ٱلۡأُنثَيَيۡنِۚ فَإِن كُنَّ نِسَآءٗ فَوۡقَ ٱثۡنَتَيۡنِ فَلَهُنَّ ثُلُثَا مَا تَرَكَۖ وَإِن كَانَتۡ وَٰحِدَةٗ فَلَهَا ٱلنِّصۡفُۚ وَلِأَبَوَيۡهِ لِكُلِّ وَٰحِدٖ مِّنۡهُمَا ٱلسُّدُسُ مِمَّا تَرَكَ إِن كَانَ لَهُۥ وَلَدٞۚ فَإِن لَّمۡ يَكُن لَّهُۥ وَلَدٞ وَوَرِثَهُۥٓ أَبَوَاهُ فَلِأُمِّهِ ٱلثُّلُثُۚ فَإِن كَانَ لَهُۥٓ إِخۡوَةٞ فَلِأُمِّهِ ٱلسُّدُسُۚ مِنۢ بَعۡدِ وَصِيَّةٖ يُوصِي بِهَآ أَوۡ دَيۡنٍۗ ءَابَآؤُكُمۡ وَأَبۡنَآؤُكُمۡ لَا تَدۡرُونَ أَيُّهُمۡ أَقۡرَبُ لَكُمۡ نَفۡعٗاۚ فَرِيضَةٗ مِّنَ ٱللَّهِۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمٗا
11.   (ሰዎች ሆይ) አላህ በልጆቻችሁ ውርስ (በሚከተለው መልኩ) ያዛችኋል:: ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ያህል አለው:: (ሁለት ወይም) ከሁለት በላይ የሆኑ ሴቶች ልጆች ብቻ ወራሽ ቢሆኑ ለእነርሱ (ሟቹ) ከተወው (ሀብት) ከሶስት ሁለት እጁ ያገኛሉ (አላቸው):: አንዲት ሴት ወራሽ ብትሆን ደግሞ ለእርሷ የሀብቱ ግማሽ አላት:: ለሟቹ ልጅ ካለው ለአባቱና ለእናቱ ከሁለቱ ለእያንዳንዱ ከስድስት አንድ አላቸው:: ለእርሱ ልጅ ባይኖረውና ወላጆቹ ብቻ ቢወርሱት ለእናቱ ሲሶው አላት:: ለእርሱም ወንድሞችና እህቶች ቢኖሩት ለእናቱ ከስድስት አንድ አላት:: (ይህም ውርስ) የሚከፋፈለው ከተናዘዘው ኑዛዜ ወይም ከእዳው ክፍያ በኋላ ነው:: አባቶቻችሁና ልጆቻችሁ ለእናንተ በመጥቀም ማንኛቸው ይበልጥ ቅርብ እንደሆኑ አታውቁም:: ይህም ከአላህ የተደነገገ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነዉና::
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 婦人章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる