Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

対訳 章: 婦人章   節:
وَٱلَّٰتِي يَأۡتِينَ ٱلۡفَٰحِشَةَ مِن نِّسَآئِكُمۡ فَٱسۡتَشۡهِدُواْ عَلَيۡهِنَّ أَرۡبَعَةٗ مِّنكُمۡۖ فَإِن شَهِدُواْ فَأَمۡسِكُوهُنَّ فِي ٱلۡبُيُوتِ حَتَّىٰ يَتَوَفَّىٰهُنَّ ٱلۡمَوۡتُ أَوۡ يَجۡعَلَ ٱللَّهُ لَهُنَّ سَبِيلٗا
15. እነዚያ ከሴቶቻችሁ መካከል ዝሙትን የሚሰሩ በእነርሱ ላይ ከናንተ የሆነን አራት ታማኝ ወንዶችን አስመስክሩባቸው:: ከመሰከሩባቸዉም ሞት እስከሚደርስባቸው ወይም አላህ ለእነርሱ ሌላ መንገድን እስከሚያደርግ ድረስ በቤቶች ውስጥ ያዟቸው(እሰሯቸው::)
アラビア語 クルアーン注釈:
وَٱلَّذَانِ يَأۡتِيَٰنِهَا مِنكُمۡ فَـَٔاذُوهُمَاۖ فَإِن تَابَا وَأَصۡلَحَا فَأَعۡرِضُواْ عَنۡهُمَآۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ تَوَّابٗا رَّحِيمًا
16. እነዚያ ከእናንተ ውስጥ ዝሙትን የሚሰሩትን አሰቃዩዋቸው (በሚገባ ቅጧቸው):: ቢጸጸቱና ስራቸውን ቢያሳምሩ ግን እነርሱን ተዋቸው (አታሰቃዩዋቸው።) አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና።
アラビア語 クルアーン注釈:
إِنَّمَا ٱلتَّوۡبَةُ عَلَى ٱللَّهِ لِلَّذِينَ يَعۡمَلُونَ ٱلسُّوٓءَ بِجَهَٰلَةٖ ثُمَّ يَتُوبُونَ مِن قَرِيبٖ فَأُوْلَٰٓئِكَ يَتُوبُ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمٗا
17. ጸጸትን መቀበል ከአላህ በኩል ለእነዚያ ኃጢአትን በስህተት ለሚሰሩና ከዚያም ወዲያውኑ ለሚጸጸቱ ነው:: እነዚያንማ አላህ ከእነርሱ ጸጸትን ይቀበላል:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና፣
アラビア語 クルアーン注釈:
وَلَيۡسَتِ ٱلتَّوۡبَةُ لِلَّذِينَ يَعۡمَلُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ حَتَّىٰٓ إِذَا حَضَرَ أَحَدَهُمُ ٱلۡمَوۡتُ قَالَ إِنِّي تُبۡتُ ٱلۡـَٰٔنَ وَلَا ٱلَّذِينَ يَمُوتُونَ وَهُمۡ كُفَّارٌۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَعۡتَدۡنَا لَهُمۡ عَذَابًا أَلِيمٗا
18. ጸጸትን መቀበል ለእነዚያ ኃጢአቶችን ለሚሰሩና ልክ ሞት በመጣባቸው ጊዜ «አሁን ተጸጸትኩ።» ለሚሉና ለእነዚያም ከሓዲያን ሆነው ለሚሞቱ አይደለም:: ለእነርሱማ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል።
アラビア語 クルアーン注釈:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا يَحِلُّ لَكُمۡ أَن تَرِثُواْ ٱلنِّسَآءَ كَرۡهٗاۖ وَلَا تَعۡضُلُوهُنَّ لِتَذۡهَبُواْ بِبَعۡضِ مَآ ءَاتَيۡتُمُوهُنَّ إِلَّآ أَن يَأۡتِينَ بِفَٰحِشَةٖ مُّبَيِّنَةٖۚ وَعَاشِرُوهُنَّ بِٱلۡمَعۡرُوفِۚ فَإِن كَرِهۡتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰٓ أَن تَكۡرَهُواْ شَيۡـٔٗا وَيَجۡعَلَ ٱللَّهُ فِيهِ خَيۡرٗا كَثِيرٗا
19. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ሆናችሁ ልትወርሱና ግልጽ የሆነ መጥፎ ስራ ካልሰሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱባቸውና ልታጉላሏዋቸው አይፈቀድላችሁም:: በመልካም ተኗኗሯቸው:: ብትጠሏቸዉም እንኳን ታገሱ:: አንድ ነገር ብትጠሉትም አላህ በእርሱ ዉስጥ ብዙ ደግ ነገሮችን ሊያደርግላችሁ ይችላልና::
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 婦人章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる