Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次


対訳 章: 婦人章   節:
وَإِنۡ أَرَدتُّمُ ٱسۡتِبۡدَالَ زَوۡجٖ مَّكَانَ زَوۡجٖ وَءَاتَيۡتُمۡ إِحۡدَىٰهُنَّ قِنطَارٗا فَلَا تَأۡخُذُواْ مِنۡهُ شَيۡـًٔاۚ أَتَأۡخُذُونَهُۥ بُهۡتَٰنٗا وَإِثۡمٗا مُّبِينٗا
20. (ባሎች ሆይ!) በሚስት ቦታ ሌላ ሚስትን ለመለወጥ ብትፈልጉ (ለምትፈታው ሴት ቀደም ሲል) ብዙን ገንዘብ የሰጣችኋት እንደሆነ ከእርሷ ምንንም አትውሰዱባት:: በመበደልና ግልጽ በሆነ ኃጢአት ትወስዱታላችሁን?
アラビア語 クルアーン注釈:
وَكَيۡفَ تَأۡخُذُونَهُۥ وَقَدۡ أَفۡضَىٰ بَعۡضُكُمۡ إِلَىٰ بَعۡضٖ وَأَخَذۡنَ مِنكُم مِّيثَٰقًا غَلِيظٗا
21. ከፊላችሁ ወደ ከፊሉ የደረሰ ሲሆንና ከናንተ ላይም (ሴቶች) የጠበቀ ቃል ኪዳንን የያዙባችሁ ሲሆኑ እንዴት ትወስዱታላችሁ?
アラビア語 クルアーン注釈:
وَلَا تَنكِحُواْ مَا نَكَحَ ءَابَآؤُكُم مِّنَ ٱلنِّسَآءِ إِلَّا مَا قَدۡ سَلَفَۚ إِنَّهُۥ كَانَ فَٰحِشَةٗ وَمَقۡتٗا وَسَآءَ سَبِيلًا
22. (ወንዶች ሆይ!) ከሴቶች መካከል አባቶቻችሁ ያገቧቸውን አታግቡ። ያለፈው ሲቀር። እርሱ መጥፎና የተጠላ ስራ ነውና። መንገድነቱም ከፋ።
アラビア語 クルアーン注釈:
حُرِّمَتۡ عَلَيۡكُمۡ أُمَّهَٰتُكُمۡ وَبَنَاتُكُمۡ وَأَخَوَٰتُكُمۡ وَعَمَّٰتُكُمۡ وَخَٰلَٰتُكُمۡ وَبَنَاتُ ٱلۡأَخِ وَبَنَاتُ ٱلۡأُخۡتِ وَأُمَّهَٰتُكُمُ ٱلَّٰتِيٓ أَرۡضَعۡنَكُمۡ وَأَخَوَٰتُكُم مِّنَ ٱلرَّضَٰعَةِ وَأُمَّهَٰتُ نِسَآئِكُمۡ وَرَبَٰٓئِبُكُمُ ٱلَّٰتِي فِي حُجُورِكُم مِّن نِّسَآئِكُمُ ٱلَّٰتِي دَخَلۡتُم بِهِنَّ فَإِن لَّمۡ تَكُونُواْ دَخَلۡتُم بِهِنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيۡكُمۡ وَحَلَٰٓئِلُ أَبۡنَآئِكُمُ ٱلَّذِينَ مِنۡ أَصۡلَٰبِكُمۡ وَأَن تَجۡمَعُواْ بَيۡنَ ٱلۡأُخۡتَيۡنِ إِلَّا مَا قَدۡ سَلَفَۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ غَفُورٗا رَّحِيمٗا
23. (ወንዶች ሆይ!) እናቶቻችሁ፤ ሴት ልጆቻችሁ፤ እህቶቻችሁ፤ አክስቶቻችሁ (የአባቶቻችሁ እህቶች)፣ አክስቶቻችሁ (የእናቶቻችሁ እህቶች)፤ የወንድም ሴት ልጆች፤ የእህት ሴት ልጆች፤ እነዚያም ያጠቧችሁ የጡት እናቶቻችሁ፤ የጡት እህቶቻችሁ፤ የሚስቶቻችሁ እናቶች፤ እነዚያም ከጉያዎቻችሁ ያሉት የእነዚያ ግብረ ስጋ ግንኙነት የፈጸማችሁባቸው ሚስቶቻችሁ ሴት ልጆች ልታገቧቸው በእናንተ ላይ እርም ተደረጉባችሁ:: ግብረ ስጋ ግንኙነት ያልፈጸማችሁባቸው የሚስቶቻችሁ ሴት ልጆቻቸውን ብታገቡ ግን በእናንተ ላይ ኃጢአት የለባችሁም:: የእነዚያ ከጀርባዎቻችሁ የሆኑት ወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶችም ሁለት እህትማማቾችን በአንድ መሰብሰብም እንደዚሁ እርም ነው:: ከዚህ በፊት ያለፈው ሲቀር:: እርሱንስ ተምራችኋል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 婦人章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる