Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

対訳 章: 雌牛章   節:
وَإِذۡ أَخَذۡنَا مِيثَٰقَكُمۡ لَا تَسۡفِكُونَ دِمَآءَكُمۡ وَلَا تُخۡرِجُونَ أَنفُسَكُم مِّن دِيَٰرِكُمۡ ثُمَّ أَقۡرَرۡتُمۡ وَأَنتُمۡ تَشۡهَدُونَ
84. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) የሕዝቦቻችሁን ደም አታፍስሱ:: ወገኖቻችሁን ከመኖሪያ አገሮቻቸው አታስወጡ በማለት የጠበቀ ቃልኪዳናችሁን በያዝንባችሁ ጊዜ (የሆነውን) አስታውሱ:: ከዚያም በቃል ኪዳኑ ትክክለኛነት አጸናችሁ::እናንተም በዚሁም ትመሰክራላችሁ፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
ثُمَّ أَنتُمۡ هَٰٓؤُلَآءِ تَقۡتُلُونَ أَنفُسَكُمۡ وَتُخۡرِجُونَ فَرِيقٗا مِّنكُم مِّن دِيَٰرِهِمۡ تَظَٰهَرُونَ عَلَيۡهِم بِٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَٰنِ وَإِن يَأۡتُوكُمۡ أُسَٰرَىٰ تُفَٰدُوهُمۡ وَهُوَ مُحَرَّمٌ عَلَيۡكُمۡ إِخۡرَاجُهُمۡۚ أَفَتُؤۡمِنُونَ بِبَعۡضِ ٱلۡكِتَٰبِ وَتَكۡفُرُونَ بِبَعۡضٖۚ فَمَا جَزَآءُ مَن يَفۡعَلُ ذَٰلِكَ مِنكُمۡ إِلَّا خِزۡيٞ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يُرَدُّونَ إِلَىٰٓ أَشَدِّ ٱلۡعَذَابِۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ
85. ከዚያም ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ የምትገድሉ፤ ከናንተም መካከል የሆኑ ሕዝቦችን በኃጢአትና በመበደል ላይ በመተባበር ከአገሮቻቸው የምታስወጡ እናንተው ራሳችሁ ናችሁ:: ምርኮኞች ሆነው ወደ እናንተ ሲመጡም ቤዛ ትሆኗቸዋላችሁ:: እነርሱን ከመኖሪያ ክልላቸው ማባረሩ በእናንተ ላይ የተከለከለ ነው:: በመጽሐፉ በከፊሉ አምናችሁ በሌላው ትክዳላችሁን? ከእናንተ መካከል ይህንን ጸያፍ ተግባር የሚሰራ ሰው ሁሉ ቅጣቱ በቅርቢቱ ሕይወት ውርደት አንጂ ሌላ አይደለም:: በትንሳኤ ቀንም ወደ ብርቱ ቅጣት ይመለሳሉ። አላህ ከምትሰሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም።
アラビア語 クルアーン注釈:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ ٱشۡتَرَوُاْ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا بِٱلۡأٓخِرَةِۖ فَلَا يُخَفَّفُ عَنۡهُمُ ٱلۡعَذَابُ وَلَا هُمۡ يُنصَرُونَ
86. እነዚያ ቅርቢቱን ሕይወት በመጨረሻይቱ ዓለም የለወጡ ናቸው። ከእነርሱ ላይም ቅጣቱ ምንጊዜም አይቀለልላቸዉም:: እርዳታም ከማንም አያገኙም።
アラビア語 クルアーン注釈:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ وَقَفَّيۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِۦ بِٱلرُّسُلِۖ وَءَاتَيۡنَا عِيسَى ٱبۡنَ مَرۡيَمَ ٱلۡبَيِّنَٰتِ وَأَيَّدۡنَٰهُ بِرُوحِ ٱلۡقُدُسِۗ أَفَكُلَّمَا جَآءَكُمۡ رَسُولُۢ بِمَا لَا تَهۡوَىٰٓ أَنفُسُكُمُ ٱسۡتَكۡبَرۡتُمۡ فَفَرِيقٗا كَذَّبۡتُمۡ وَفَرِيقٗا تَقۡتُلُونَ
87. ለሙሳ መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው:: ከርሱ በኋላም ሌሎች መልዕክተኞችን ልከናል:: የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ተዐምራትን ሰጠነው:: ቅዱስ መንፈስ (ጅብሪል) በሚባለው መላአክ አበረታነው:: ነፍሶቻችሁ በማትወደው ነገር መልዕክተኛው በመጣላችሁ ቁጥር እነርሱን ከመከተል ይልቅ በትዕቢት ከፊሉን አስተባበላችሁ:: ከፊሉን ደግሞ ትገድላላችሁን?
アラビア語 クルアーン注釈:
وَقَالُواْ قُلُوبُنَا غُلۡفُۢۚ بَل لَّعَنَهُمُ ٱللَّهُ بِكُفۡرِهِمۡ فَقَلِيلٗا مَّا يُؤۡمِنُونَ
88. “ልቦቻችን ድፍኖች ናቸው” አሉ:: (እውነታው ግን ይህ አይደለም)። አላህ በክህደታቸው ምክንያት ረገማቸው። በመሆኑም ጥቂትን እንጂ አያምኑም።
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 雌牛章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる