Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

対訳 章: 雌牛章   節:
سَلۡ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ كَمۡ ءَاتَيۡنَٰهُم مِّنۡ ءَايَةِۭ بَيِّنَةٖۗ وَمَن يُبَدِّلۡ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَتۡهُ فَإِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ
211. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የኢስራኢል ልጆችን ምን ያህል ግልጽ ተዐምር እንደሰጣናቸው ጠይቃቸው:: የአላህን ጸጋ ከመጣለት በኋላ ለሚለውጥ (ሰው አላህ ይቀጠዋል) አላህ ቅጣተ ብርቱ ነው።
アラビア語 クルアーン注釈:
زُيِّنَ لِلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا وَيَسۡخَرُونَ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْۘ وَٱلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ فَوۡقَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ وَٱللَّهُ يَرۡزُقُ مَن يَشَآءُ بِغَيۡرِ حِسَابٖ
212. ለእነዚያ ለካዱት ባመኑት የሚሳለቁ ሲሆኑ ቅርቢቱ ሕይወት ተሸለመችላቸው:: እነዚያ አላህን የሚፈሩት በትንሳኤ ቀን ከበላያቸው ናቸው:: አላህም ለፈለገው ገጸ በረከቱን ያለገደብ ይሰጣልና::
アラビア語 クルアーン注釈:
كَانَ ٱلنَّاسُ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ فَبَعَثَ ٱللَّهُ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ وَأَنزَلَ مَعَهُمُ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ لِيَحۡكُمَ بَيۡنَ ٱلنَّاسِ فِيمَا ٱخۡتَلَفُواْ فِيهِۚ وَمَا ٱخۡتَلَفَ فِيهِ إِلَّا ٱلَّذِينَ أُوتُوهُ مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَتۡهُمُ ٱلۡبَيِّنَٰتُ بَغۡيَۢا بَيۡنَهُمۡۖ فَهَدَى ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لِمَا ٱخۡتَلَفُواْ فِيهِ مِنَ ٱلۡحَقِّ بِإِذۡنِهِۦۗ وَٱللَّهُ يَهۡدِي مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٍ
213. ሰዎች ሁሉ (አላህን አንድ በማድረግ) አንድ ሕዝብ ነበሩ:: (ከዚያም ተለያዩ):: ከዚያም አላህ ነብያትን ለመልካም ሰዎች በገነት አብሳሪዎችና ለመጥፎ ሰዎች ደግሞ ከእሳት አስጠንቃቂዎች አድርጎ ላከ:: ከነሱ ጋርም ከሰዎቹ መካከል በዚያ እነርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ መጽሐፍትን በእውነት አወረደ:: በእርሱ ግልጽ አስረጂዎች ከመጡላቸው በኋላ በመካከላቸው በተፈጠረው ምቀኝነት ሰበብ እነዚያው መጽሐፍትን የተሰጡት ሰዎች እንጂ አልተለያዩበትም:: አላህ እነዚያን በአላህ ያመኑትን ሰዎች በእነርሱ የተለያዩበትን እውነታ ይገነዘቡ ዘንድ በፈቃዱ መራቸው:: አላህ የሚሻውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል።
アラビア語 クルアーン注釈:
أَمۡ حَسِبۡتُمۡ أَن تَدۡخُلُواْ ٱلۡجَنَّةَ وَلَمَّا يَأۡتِكُم مَّثَلُ ٱلَّذِينَ خَلَوۡاْ مِن قَبۡلِكُمۖ مَّسَّتۡهُمُ ٱلۡبَأۡسَآءُ وَٱلضَّرَّآءُ وَزُلۡزِلُواْ حَتَّىٰ يَقُولَ ٱلرَّسُولُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ مَتَىٰ نَصۡرُ ٱللَّهِۗ أَلَآ إِنَّ نَصۡرَ ٱللَّهِ قَرِيبٞ
214. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት አማኞችን ያጋጠመ መከራ የመሰለ ሳይመጣባችሁ ገነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልዕክተኛውና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት «የአላህ እርዳታ መቼ ነው?» እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ደረሰባቸው:: ተርበደበዱም። (ሙስሊሞች ሆይ! ) አስተውሉ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው (አልናቸው)።
アラビア語 クルアーン注釈:
يَسۡـَٔلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَۖ قُلۡ مَآ أَنفَقۡتُم مِّنۡ خَيۡرٖ فَلِلۡوَٰلِدَيۡنِ وَٱلۡأَقۡرَبِينَ وَٱلۡيَتَٰمَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِۗ وَمَا تَفۡعَلُواْ مِنۡ خَيۡرٖ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِهِۦ عَلِيمٞ
215. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምንን እንደሚለግሱ ይጠይቁሃል። «ከየትኛዉም ሀብት የምትለግሱት ለወላጆች፣ ለቅርብ ዘመዶች፣ ለየቲሞች፣ ለድሆችና ለመንገደኞች (ሊሆን ይገባል።) ከበጎ ነገርም ማንኛውንም ብትሰሩ አላህ እርሱን አዋቂ ነው።»በላቸው፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 雌牛章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる