Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次


対訳 章: 雌牛章   節:
كُتِبَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡقِتَالُ وَهُوَ كُرۡهٞ لَّكُمۡۖ وَعَسَىٰٓ أَن تَكۡرَهُواْ شَيۡـٔٗا وَهُوَ خَيۡرٞ لَّكُمۡۖ وَعَسَىٰٓ أَن تُحِبُّواْ شَيۡـٔٗا وَهُوَ شَرّٞ لَّكُمۡۚ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ
216. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከሓዲያንን መጋደል በእናንተ ዘንድ የሚጠላ ቢሆንም በእናንተ ላይ በግዴታነት ተደነገገ:: አንድ ነገር ለእናንተ ጥሩ ቢሆንም ምናልባት ትጠሉት ይሆናል:: አንድንም ነገር እርሱ ለእናንተ መጥፎ ሆኖ እያለ ትወዱት ይሆናል:: አላህም የሚሻላችሁን ያውቃል:: እናንተ ግን አታውቁም::
アラビア語 クルアーン注釈:
يَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلشَّهۡرِ ٱلۡحَرَامِ قِتَالٖ فِيهِۖ قُلۡ قِتَالٞ فِيهِ كَبِيرٞۚ وَصَدٌّ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ وَكُفۡرُۢ بِهِۦ وَٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ وَإِخۡرَاجُ أَهۡلِهِۦ مِنۡهُ أَكۡبَرُ عِندَ ٱللَّهِۚ وَٱلۡفِتۡنَةُ أَكۡبَرُ مِنَ ٱلۡقَتۡلِۗ وَلَا يَزَالُونَ يُقَٰتِلُونَكُمۡ حَتَّىٰ يَرُدُّوكُمۡ عَن دِينِكُمۡ إِنِ ٱسۡتَطَٰعُواْۚ وَمَن يَرۡتَدِدۡ مِنكُمۡ عَن دِينِهِۦ فَيَمُتۡ وَهُوَ كَافِرٞ فَأُوْلَٰٓئِكَ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
217. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በተከበረው ወር ስለመጋደል ይጠይቁሃል። «በእነርሱ ውስጥ መጋደል ትልቅ ኃጢአት ነው:: ግን ከአላህ መንገድ ሰዎችን መከልከል፤ በእርሱም መካድ፤ ከተከበረው መስጊድ ማገድ፤ ባለቤቶቹንም ከእርሱ ማፈናቀል አላህ ዘንድ ይበልጥ የተለቀ ወንጀል ነው:: ፈተናም (በአላህ ማጋራትም) ከመግደል ይበልጥ ከባድ ነው» በላቸው። ከሓዲያን ቢችሉ ከሃይማኖታችሁ እስኪመልሷችሁ ድረስ የሚዋጓችሁ ከመሆን አይቦዝኑም:: ከናንተ ውስጥ ከሀይማኖቱ የሚመለስና እርሱ ከሃዲ ሆኖ የሚሞት ሁሉ እነዚያ በቅርቢቱ ሀገርም ሆነ በመጨረሻይቱ ሀገር በጎ ስራቸው ተበላሸች:: እነዚህ የእሳት ጓዶች ናቸው:: በእርሷም ውስጥ ለዘላለም ይዝወትራሉ።
アラビア語 クルアーン注釈:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَٱلَّذِينَ هَاجَرُواْ وَجَٰهَدُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ أُوْلَٰٓئِكَ يَرۡجُونَ رَحۡمَتَ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
218. እነዚያ ያመኑና ከሀገራቸው የተሰደዱ፤ በአላህ መንገድ ላይም የተጋደሉ፤ እነዚያ የአላህን እዝነት ይከጅላሉ:: አላህም እጅግ መሀሪና አዛኝ ነውና፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
۞ يَسۡـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلۡخَمۡرِ وَٱلۡمَيۡسِرِۖ قُلۡ فِيهِمَآ إِثۡمٞ كَبِيرٞ وَمَنَٰفِعُ لِلنَّاسِ وَإِثۡمُهُمَآ أَكۡبَرُ مِن نَّفۡعِهِمَاۗ وَيَسۡـَٔلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَۖ قُلِ ٱلۡعَفۡوَۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمُ ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّكُمۡ تَتَفَكَّرُونَ
219. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አዕምሮን ስለሚያሰክር መጠጥና ስለ ቁማር ይጠይቁሃል:: «በሁለቱም ትልቅ ኃጢአትነትና ለሰዎችም ጥቅም አለባቸው:: ኃጢአታቸው ግን ከጥቅማቸው በጣም የገዘፈ ነው።» በላቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምንን እንደሚመጸውቱም (መጠኑን) ይጠይቁሀል:: «የተረፋችሁን መጽውቱ።» በላቸው:: እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 雌牛章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる