Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

対訳 章: 雌牛章   節:
ٱللَّهُ وَلِيُّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ يُخۡرِجُهُم مِّنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِۖ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَوۡلِيَآؤُهُمُ ٱلطَّٰغُوتُ يُخۡرِجُونَهُم مِّنَ ٱلنُّورِ إِلَى ٱلظُّلُمَٰتِۗ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
257. አላህ የአማኞች ወዳጅ ነው:: ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል:: እነዚያ አላህን የካዱት ግን ረዳቶቻቸው ጣኦታት ናቸው:: ከብርሃን ወደ ጨለማ ይመሯቸዋል:: እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው::
アラビア語 クルアーン注釈:
أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِي حَآجَّ إِبۡرَٰهِـۧمَ فِي رَبِّهِۦٓ أَنۡ ءَاتَىٰهُ ٱللَّهُ ٱلۡمُلۡكَ إِذۡ قَالَ إِبۡرَٰهِـۧمُ رَبِّيَ ٱلَّذِي يُحۡيِۦ وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا۠ أُحۡيِۦ وَأُمِيتُۖ قَالَ إِبۡرَٰهِـۧمُ فَإِنَّ ٱللَّهَ يَأۡتِي بِٱلشَّمۡسِ مِنَ ٱلۡمَشۡرِقِ فَأۡتِ بِهَا مِنَ ٱلۡمَغۡرِبِ فَبُهِتَ ٱلَّذِي كَفَرَۗ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
258. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን አላህ ንግስናን ስለ ሰጠውና በጌታው ጉዳይ በኢብራሂም ላይ ክርክር ስለ ከፈተው ሰው (ታሪክ) መረጃ አላየህምን? ኢብራሂም፡-‹‹ጌታዬ ያ የፈለገውን ሕያው የሚያደርግና የፈለገውን የሚገድል ነው›› ሲለው «እኔም የፈለኩትን ህያው አደርጋለሁ፤ የፈለኩትን እገድላለሁ» አለ:: ኢብራሂምም፡- «አላህ ጸሐይን በምስራቅ በኩል ያወጣል:: እስኪ አንተ ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው:: ያም የካደ ሰው ዋለለ (መልስ አጣ):: አላህ ግፈኛ ሕዝቦችን ሁሉ አይመራምና::
アラビア語 クルアーン注釈:
أَوۡ كَٱلَّذِي مَرَّ عَلَىٰ قَرۡيَةٖ وَهِيَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا قَالَ أَنَّىٰ يُحۡيِۦ هَٰذِهِ ٱللَّهُ بَعۡدَ مَوۡتِهَاۖ فَأَمَاتَهُ ٱللَّهُ مِاْئَةَ عَامٖ ثُمَّ بَعَثَهُۥۖ قَالَ كَمۡ لَبِثۡتَۖ قَالَ لَبِثۡتُ يَوۡمًا أَوۡ بَعۡضَ يَوۡمٖۖ قَالَ بَل لَّبِثۡتَ مِاْئَةَ عَامٖ فَٱنظُرۡ إِلَىٰ طَعَامِكَ وَشَرَابِكَ لَمۡ يَتَسَنَّهۡۖ وَٱنظُرۡ إِلَىٰ حِمَارِكَ وَلِنَجۡعَلَكَ ءَايَةٗ لِّلنَّاسِۖ وَٱنظُرۡ إِلَى ٱلۡعِظَامِ كَيۡفَ نُنشِزُهَا ثُمَّ نَكۡسُوهَا لَحۡمٗاۚ فَلَمَّا تَبَيَّنَ لَهُۥ قَالَ أَعۡلَمُ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
259. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወይም ያንን ሙሉ በሙሉ በፈራረሰች ከተማ ያለፈውን ሰው ተሞክሮ አላገናዘብክምን? ‹‹ይህችን ከተማ ከሞተች በኃላ አላህ እንዴት ሕያው ያደርጋታል? አለ:: ከዚያ አላህ ገደለውና መቶ ዓመትን አቆየው:: ከዚያ አስነሳው «ምን ያህል ቆየህ?» አለው:: «አንድ ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆይቻለሁ» አለ:: «ይልቁንም መቶ ዓመት ነው የቆየኸው:: ወደ ምግብህና ወደ መጠጥህም ተመልከት:: አንዱም አልተለወጠም:: ወደ አህያህም ተመልከት:: ለሰው ልጅም ተዐምር ልናደርግህ ዘንድ ይህንን ሰራን፤ ወደ አጽሞቿም እንዴት እንደምናስነሳት ከዚያ ስጋን እንዴት እንደምናለብሳት ተመልከት።» አለው:: ለእርሱም ማስረጃ በገለጸለት ጊዜ ‹‹አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አውቃለሁ›› አለ::
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 雌牛章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる