Check out the new design

クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー * - 対訳の目次

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

対訳 章: 雌牛章   節:
ٱلۡحَجُّ أَشۡهُرٞ مَّعۡلُومَٰتٞۚ فَمَن فَرَضَ فِيهِنَّ ٱلۡحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِي ٱلۡحَجِّۗ وَمَا تَفۡعَلُواْ مِنۡ خَيۡرٖ يَعۡلَمۡهُ ٱللَّهُۗ وَتَزَوَّدُواْ فَإِنَّ خَيۡرَ ٱلزَّادِ ٱلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُونِ يَٰٓأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِ
197. ሐጅ የሚፈጸመው በተወሰኑ የታወቁ ወራት ነው:: እናም በእነርሱ ውስጥ ሐጅን ለመስራት ግዴታ የገባ ሰው በሐጅ ክንውን ውስጥ እያለ ሴትን መገናኘት፤ በአላህ ላይ ማመጽና ክርክር አያደርግም:: (ሙስሊሞች ሆይ!)የምትሰሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል። ስንቅም ያዙ:: ከስንቅ ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው:: የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! እኔን ብቻ ፍሩኝ።
アラビア語 クルアーン注釈:
لَيۡسَ عَلَيۡكُمۡ جُنَاحٌ أَن تَبۡتَغُواْ فَضۡلٗا مِّن رَّبِّكُمۡۚ فَإِذَآ أَفَضۡتُم مِّنۡ عَرَفَٰتٖ فَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ عِندَ ٱلۡمَشۡعَرِ ٱلۡحَرَامِۖ وَٱذۡكُرُوهُ كَمَا هَدَىٰكُمۡ وَإِن كُنتُم مِّن قَبۡلِهِۦ لَمِنَ ٱلضَّآلِّينَ
198. በሐጅ ጊዜ (በስራ) ከጌታችሁ ችሮታን በመፈለጋችሁ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም:: ከአረፋት በተንቀሳቀሳችሁም ጊዜ መሸዐረል ሀራም ዘንድ ስትደርሱ አላህን አውሱ:: ወደ ቀናው የኢስላም መንገድ ስለመራችሁም አውሱት:: ቀደም ሲል በእርግጥ ከተሳሳቾች ነበራችሁ።
アラビア語 クルアーン注釈:
ثُمَّ أَفِيضُواْ مِنۡ حَيۡثُ أَفَاضَ ٱلنَّاسُ وَٱسۡتَغۡفِرُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
199. ከዚያ ሰዎች ከተንቀሳቀሱበት ስፍራ ተንቀሳቀሱ :: የአላህንም ምህረት ለምኑ:: አላህ በእጅጉ መሀሪና አዛኝ ነውና፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
فَإِذَا قَضَيۡتُم مَّنَٰسِكَكُمۡ فَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ كَذِكۡرِكُمۡ ءَابَآءَكُمۡ أَوۡ أَشَدَّ ذِكۡرٗاۗ فَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَقُولُ رَبَّنَآ ءَاتِنَا فِي ٱلدُّنۡيَا وَمَا لَهُۥ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِنۡ خَلَٰقٖ
200. የሐጅ ስራዎቻችሁን በፈጸማችሁ ጊዜ አባቶቻችሁን እንደምታወሱ ወይም ከእርሱም ይበልጥ በበረታ አላህን አውሱ:: ከሰዎችም መካከል፡- «ጌታችን ሆይ! በምድረ ዓለም መልካም እድልን ስጠን።» የሚል ሰው አለ:: ለእርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም ድርሻ የለዉም::
アラビア語 クルアーン注釈:
وَمِنۡهُم مَّن يَقُولُ رَبَّنَآ ءَاتِنَا فِي ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٗ وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِ حَسَنَةٗ وَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ
201. ከእነርሱም መካከል «ጌታችን ሆይ! በምድር ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን) በመጨረሻይቱ ሀገርም ደግን ነገር (ገነትን) ስጠን:: ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።» የሚሉ አሉ።
アラビア語 クルアーン注釈:
أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ نَصِيبٞ مِّمَّا كَسَبُواْۚ وَٱللَّهُ سَرِيعُ ٱلۡحِسَابِ
202. እነዚያ ከሰሩት በጎ ስራ ድርሻ አላቸው:: አላህም ምርመራው ፈጣን ነው፡፡
アラビア語 クルアーン注釈:
 
対訳 章: 雌牛章
章名の目次 ページ番号
 
クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー - 対訳の目次

محمد زين زهر الدين訳。アフリカアカデミー発行。

閉じる