Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន   អាយ៉ាត់:

ኣሊ-ኢምራን

الٓمٓ
1. አሊፍ፤ ላም፤ ሚም፤
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡحَيُّ ٱلۡقَيُّومُ
2. አላህ ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: አላህ ህያው፤ በራሱ የተብቃቃና የሁሉ ነገር አስተናባሪ (የፍጡራን ተንከባካቢ) ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
نَزَّلَ عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ مُصَدِّقٗا لِّمَا بَيۡنَ يَدَيۡهِ وَأَنزَلَ ٱلتَّوۡرَىٰةَ وَٱلۡإِنجِيلَ
3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ቁርኣንን ከእርሱ በፊት ያሉትን መጽሐፍት የሚያረጋግጥ ሲሆን ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደው። ከቁርኣን በፊትም ለሰዎች መሪ አድርጎ ተውራትንና ኢንጅልን አውርዷል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مِن قَبۡلُ هُدٗى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ ٱلۡفُرۡقَانَۗ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ لَهُمۡ عَذَابٞ شَدِيدٞۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٞ ذُو ٱنتِقَامٍ
4. ከቁርኣን በፊትም ለሰዎች መሪ አድርጎ ተውራትንና ኢንጅልን አውርዷል። (በእውነትና በውሸት መካከል መለያ የሆነውን) ፉርቃንንም አወረደ። እነዚያ በአላህ አናቅጽ የካዱ ሁሉ ብርቱ ቅጣት አለባቸው። አላህ ሁሉን አሸናፊ፤ አስተባባዮችን ተበቃይም ነውና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَخۡفَىٰ عَلَيۡهِ شَيۡءٞ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فِي ٱلسَّمَآءِ
5. አላህ በምድርም ሆነ በሰማይ ምንም ነገር አይሸሸግበትም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
هُوَ ٱلَّذِي يُصَوِّرُكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡحَامِ كَيۡفَ يَشَآءُۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
6. በማህጸኖች ውስጥ እንደፈለገው አድርጎ የሚቀርፃችሁ እርሱው ነው። ከእርሱ ከአሸናፊዉና ከጥበበኛው ጌታ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ በፍጹም የለም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنزَلَ عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ مِنۡهُ ءَايَٰتٞ مُّحۡكَمَٰتٌ هُنَّ أُمُّ ٱلۡكِتَٰبِ وَأُخَرُ مُتَشَٰبِهَٰتٞۖ فَأَمَّا ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمۡ زَيۡغٞ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَٰبَهَ مِنۡهُ ٱبۡتِغَآءَ ٱلۡفِتۡنَةِ وَٱبۡتِغَآءَ تَأۡوِيلِهِۦۖ وَمَا يَعۡلَمُ تَأۡوِيلَهُۥٓ إِلَّا ٱللَّهُۗ وَٱلرَّٰسِخُونَ فِي ٱلۡعِلۡمِ يَقُولُونَ ءَامَنَّا بِهِۦ كُلّٞ مِّنۡ عِندِ رَبِّنَاۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ
7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያ ባንተ ላይ መጽሐፍን-(ቁርኣንን) ያወረደ ነው:: ከመጽሐፉም ውስጥ ግልጽ የሆኑ አናቅጽ አሉ:: እነርሱም የመጽሐፉ መሰረቶች ናቸው። ሌሎች ደግሞ አሻሚ ትርጉም ያላቸው አሉ:: እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሌሎችን ለማሳሳት በማሰብና ትርጉሙን በሻቸው ለመለወጥ ሲሉ አሻሚ ትርጉም (ተመሳሳይነት) ያሏቸውን አናቅጽ ብቻ ይከታተላሉ። ትክክለኛ ትርጉማቸውን አላህ ብቻ እንጂ ሌላ ማንም አያውቀዉም:: እነዚያ በእውቀት የጠለቁት ግን «በእርሱ አምነናል። ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው።» ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶች እንጂ አይገሰጽም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
رَبَّنَا لَا تُزِغۡ قُلُوبَنَا بَعۡدَ إِذۡ هَدَيۡتَنَا وَهَبۡ لَنَا مِن لَّدُنكَ رَحۡمَةًۚ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡوَهَّابُ
8. (እነርሱም የሚሉ ናቸው:) «ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን ወደ መጥፎ አታዘንብልብን:: ካንተ ዘንድ የሆነን ችሮታ ስጠን:: አንተ በጣም ለጋስ ነህና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
رَبَّنَآ إِنَّكَ جَامِعُ ٱلنَّاسِ لِيَوۡمٖ لَّا رَيۡبَ فِيهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُخۡلِفُ ٱلۡمِيعَادَ
9. «ጌታችን ሆይ! አንተ በዚያ ለመምጣቱ ጥርጥር በሌለበት ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ:: ምን ጊዜም አላህ ቀጠሮን አያፈርስምና»::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ