Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន   អាយ៉ាត់:
هُنَالِكَ دَعَا زَكَرِيَّا رَبَّهُۥۖ قَالَ رَبِّ هَبۡ لِي مِن لَّدُنكَ ذُرِّيَّةٗ طَيِّبَةًۖ إِنَّكَ سَمِيعُ ٱلدُّعَآءِ
38. እዚያ ዘንድም ዘከርያ ጌታውን እንደዚህ በማለት ለመነ: «ጌታዬ ሆይ! ካንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለእኔ ስጠኝ:: አንተ ጸሎትን ሰሚ ነህና» አለ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَنَادَتۡهُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَهُوَ قَآئِمٞ يُصَلِّي فِي ٱلۡمِحۡرَابِ أَنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحۡيَىٰ مُصَدِّقَۢا بِكَلِمَةٖ مِّنَ ٱللَّهِ وَسَيِّدٗا وَحَصُورٗا وَنَبِيّٗا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
39. እርሱም በዱዓ ማድረጊያ ክፍል ቆሞ ዱዓ ሲያደርግ መላዕክት:- «አላህ በየህያ: ከአላህ በሆነ ቃል የሚያረጋግጥ፣ በላጭ፣ ከሴት ጋር የማይገናኝ ድንግልና ከደጋጎቹም አንዱ ሲሆን ያበስርሃል።» በማለት መላዕክት ጠሩት።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي غُلَٰمٞ وَقَدۡ بَلَغَنِيَ ٱلۡكِبَرُ وَٱمۡرَأَتِي عَاقِرٞۖ قَالَ كَذَٰلِكَ ٱللَّهُ يَفۡعَلُ مَا يَشَآءُ
40. ዘከርያም «ጌታዬ ሆይ! እኔ እርጅና የደረሰብኝ ሚስቴም መካን ስትሆን እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለ። መልአኩም: «ልክ እንደዚሁ ነው። አላህ የሚሻውን ነገር ሁሉ ይሰራልና።» አለው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ رَبِّ ٱجۡعَل لِّيٓ ءَايَةٗۖ قَالَ ءَايَتُكَ أَلَّا تُكَلِّمَ ٱلنَّاسَ ثَلَٰثَةَ أَيَّامٍ إِلَّا رَمۡزٗاۗ وَٱذۡكُر رَّبَّكَ كَثِيرٗا وَسَبِّحۡ بِٱلۡعَشِيِّ وَٱلۡإِبۡكَٰرِ
41. ዘከርያም «ጌታዬ ሆይ! ለእዚህ ነገር ምልክትን አድርግልኝ።» አለ:: «ምልክትህ ሶስት ቀን በጥቅሻ እንጂ ሰዎችን አለማናገርህ ነው:: በዚያ ጊዜ ጌታህን በብዙ አውሳ:: በማታና በጠዋትም አወድሰው።» አለው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذۡ قَالَتِ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَٰمَرۡيَمُ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصۡطَفَىٰكِ وَطَهَّرَكِ وَٱصۡطَفَىٰكِ عَلَىٰ نِسَآءِ ٱلۡعَٰلَمِينَ
42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላእክትም ባሉ ጊዜ: «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ:: ከነውሮች ሁሉ አጸዳሸ:: ከዓለማት ሴቶችም መካከል መረጠሸ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰمَرۡيَمُ ٱقۡنُتِي لِرَبِّكِ وَٱسۡجُدِي وَٱرۡكَعِي مَعَ ٱلرَّٰكِعِينَ
43. «መርየም ሆይ! ለጌታሽ ታዘዢ:: ስገጂም:: ከአጎንባሾች ጋርም ሁነሽ አጎንብሺ።» (ያለበትን ታሪክ ለህዝቦችህ አውሳ።)
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ذَٰلِكَ مِنۡ أَنۢبَآءِ ٱلۡغَيۡبِ نُوحِيهِ إِلَيۡكَۚ وَمَا كُنتَ لَدَيۡهِمۡ إِذۡ يُلۡقُونَ أَقۡلَٰمَهُمۡ أَيُّهُمۡ يَكۡفُلُ مَرۡيَمَ وَمَا كُنتَ لَدَيۡهِمۡ إِذۡ يَخۡتَصِمُونَ
44.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ታሪክ ወደ አንተ ከምናወርደው ከሩቅ ወሬ ነው:: መርየምን ማን እንደሚያሳድግ ብዕሮቻቸውን ለዕጣ በጣሉ ጊዜ አንተ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም:: በሚከራከሩም ጊዜ እነርሱ ዘንድ አልነበርክም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِذۡ قَالَتِ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَٰمَرۡيَمُ إِنَّ ٱللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٖ مِّنۡهُ ٱسۡمُهُ ٱلۡمَسِيحُ عِيسَى ٱبۡنُ مَرۡيَمَ وَجِيهٗا فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ وَمِنَ ٱلۡمُقَرَّبِينَ
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትም «መርየም ሆይ! አላህ ከእርሱ በሆነው ቃል የሚፈጠር ስሙ አል መሲህ ዒሳ የመርየም ልጅ በሚባል፤ በዚህ ዓለምም ሆነ በመጨረሻው ዓለም የተከበረና ከባለሟሎቹ አንዱ በሆነ ልጅ ያበስርሻል። (ባላት ጊዜ እዚያ ቦታ አልነበርክም) ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ