Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន   អាយ៉ាត់:
قُلۡ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَمَآ أُنزِلَ عَلَيۡنَا وَمَآ أُنزِلَ عَلَىٰٓ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡمَٰعِيلَ وَإِسۡحَٰقَ وَيَعۡقُوبَ وَٱلۡأَسۡبَاطِ وَمَآ أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَٱلنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمۡ لَا نُفَرِّقُ بَيۡنَ أَحَدٖ مِّنۡهُمۡ وَنَحۡنُ لَهُۥ مُسۡلِمُونَ
84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በአላህ አምነናል በእኛም ላይ በተወረደው በቁርኣን (በነብዩ) ኢብራሂም፣ (በነብዩ) ኢስማኢል፣ (በነብዩ) ኢስሀቅ፣ (በነብዩ) የዕቆብና በነገዶች ላይ በተወረደው፣ ለነብዩ ሙሳ ለነብዩ ዒሳና ለነብያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው ሁሉ አምነናል:: በእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም:: እኛ ለእርሱ ብቻ ታዛዦች ነን።» በል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَن يَبۡتَغِ غَيۡرَ ٱلۡإِسۡلَٰمِ دِينٗا فَلَن يُقۡبَلَ مِنۡهُ وَهُوَ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ
85. ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሁሉ ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይነት የለዉም:: እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ አንዱ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
كَيۡفَ يَهۡدِي ٱللَّهُ قَوۡمٗا كَفَرُواْ بَعۡدَ إِيمَٰنِهِمۡ وَشَهِدُوٓاْ أَنَّ ٱلرَّسُولَ حَقّٞ وَجَآءَهُمُ ٱلۡبَيِّنَٰتُۚ وَٱللَّهُ لَا يَهۡدِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلظَّٰلِمِينَ
86. ከእምነታቸውና መልዕክተኛዉም እውነት መሆኑን ከመሰከሩ፤ የተብራሩ አናቅጽም ከመጡላቸው በኋላ የካዱ ሕዝቦችን አላህ እንዴት ያቀናል? አላህ በዳዮችን ሕዝቦች አያቀናምና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أُوْلَٰٓئِكَ جَزَآؤُهُمۡ أَنَّ عَلَيۡهِمۡ لَعۡنَةَ ٱللَّهِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ وَٱلنَّاسِ أَجۡمَعِينَ
87. እነዚያን መሰሎች ቅጣታቸው የአላህ፣ የመላዕክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በእነርሱ ላይ መውረዱ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
خَٰلِدِينَ فِيهَا لَا يُخَفَّفُ عَنۡهُمُ ٱلۡعَذَابُ وَلَا هُمۡ يُنظَرُونَ
88. በውስጧ ዘወታሪዎች ሲሆኑ ቅጣቱም ከእነርሱ ላይ አይቃለልላቸዉም:: ጊዜም አይሰጡም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِلَّا ٱلَّذِينَ تَابُواْ مِنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ وَأَصۡلَحُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ
89. እነዚያ ከዚያ በኋላ ንስሀ የገቡና ስራቸውን ያሳመሩ ሁሉ ሲቀሩ፤ (አላህ እነዚህንማ ይምራቸዋል።) አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بَعۡدَ إِيمَٰنِهِمۡ ثُمَّ ٱزۡدَادُواْ كُفۡرٗا لَّن تُقۡبَلَ تَوۡبَتُهُمۡ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلضَّآلُّونَ
90. እነዚያ ከእምነታቸው በኋላ የካዱና ከዚያ ክህደትን በክህደት ላይ የጨመሩ ንሰሃቸው ፈጽሞ ተቀባይነት የለዉም:: የተሳሳቱ ማለት እነርሱው ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَمَاتُواْ وَهُمۡ كُفَّارٞ فَلَن يُقۡبَلَ مِنۡ أَحَدِهِم مِّلۡءُ ٱلۡأَرۡضِ ذَهَبٗا وَلَوِ ٱفۡتَدَىٰ بِهِۦٓۗ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ
91. እነዚያ የካዱና በክህደታቸው ላይ እንዳሉ የሞቱ፤ ከእነርሱ አንዳቸው ምድርን የሞላ ወርቅ ቤዛ ቢያቀርብም እንኳ ፈጽሞ ተቀባይነት አያገኝም:: እነዚያ ለእነርሱ የሚያሰቃይ ቅጣት አለባቸው:: ለእነርሱም (ከዚህ ቅጣት) የሚያድኗቸው ምንም ረዳቶች የሏቸዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ