Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន   អាយ៉ាត់:
ٱلَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَآ إِنَّنَآ ءَامَنَّا فَٱغۡفِرۡ لَنَا ذُنُوبَنَا وَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ
16. (እነርሱም) እነዚያ «ጌታችን ሆይ! እኛ ባንተ አመንን። ኃጢአቶቻችንን ማርልን። የእሳትን ቅጣት ጠብቀን።» የሚሉ ናቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱلصَّٰبِرِينَ وَٱلصَّٰدِقِينَ وَٱلۡقَٰنِتِينَ وَٱلۡمُنفِقِينَ وَٱلۡمُسۡتَغۡفِرِينَ بِٱلۡأَسۡحَارِ
17. እነርሱም ታጋሾች፤ እውነተኞች፤ ታዛዦች፤ ለጋሾችና በሌሊት መጨረሻዎች ሰዓታት ላይ አላህን ምህረት የሚለምኑ ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
شَهِدَ ٱللَّهُ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَأُوْلُواْ ٱلۡعِلۡمِ قَآئِمَۢا بِٱلۡقِسۡطِۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
18. አላህ (በማስተካከል) ቀጥ ያለ ሲሆን ከእርሱ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የሌለ መሆኑን መሰከረ። መላዕክትና የእውቀት ባለቤቶችም መሰከሩ። ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም:: እርሱ ሁሉን አሸናፊውና ጥበበኛው ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلۡإِسۡلَٰمُۗ وَمَا ٱخۡتَلَفَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ إِلَّا مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلۡعِلۡمُ بَغۡيَۢا بَيۡنَهُمۡۗ وَمَن يَكۡفُرۡ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلۡحِسَابِ
19. አላህ ዘንድ የተወደደው ሀይማኖት ኢስላም ብቻ ነው:: እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡ ሰዎች በመካከላቸው ባለው ምቀኝነት እውቀቱ ከመጣላቸው በኋላ እንጂ አልተለያዩም:: በአላህ አናቅጽ ለሚክድ ሁሉ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَإِنۡ حَآجُّوكَ فَقُلۡ أَسۡلَمۡتُ وَجۡهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ ٱتَّبَعَنِۗ وَقُل لِّلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡأُمِّيِّـۧنَ ءَأَسۡلَمۡتُمۡۚ فَإِنۡ أَسۡلَمُواْ فَقَدِ ٱهۡتَدَواْۖ وَّإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنَّمَا عَلَيۡكَ ٱلۡبَلَٰغُۗ وَٱللَّهُ بَصِيرُۢ بِٱلۡعِبَادِ
20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢከራከሩህም «ፊቴን ለአላህ ብቻ ሰጠሁ። የተከተሉኝም እንደዚሁ ለአላህ ብቻ ሰጡ።» በላቸው:: ለእነዚያም መጽሐፉን ለተሰጡ ሰዎችና ለመሃይማኑ (ዐረቦች)፡- «ሰለማችሁን?» በላቸው:: ቢሰልሙም በእርግጥ ወደቀናው መንገድ ተመሩ:: እምቢ ቢሉ ግን ባንተ ላይ ያለብህ መልዕክትን ማድረስ ብቻ ነው:: አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَكۡفُرُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَيَقۡتُلُونَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ بِغَيۡرِ حَقّٖ وَيَقۡتُلُونَ ٱلَّذِينَ يَأۡمُرُونَ بِٱلۡقِسۡطِ مِنَ ٱلنَّاسِ فَبَشِّرۡهُم بِعَذَابٍ أَلِيمٍ
21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ አናቅጽ የሚክዱ፤ ነብያትንም ያለ አግባብ የሚገድሉ፤ ከሰዎችም ውስጥ እነዚያን በትክክለኛነት የሚያዙትን የሚገድሉ በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ
22. እነዚያ በቅርቢቱም ሆን በመጨረሻይቱ ዓለም ስራዎቻቸው የተበላሹ ናቸው:: ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ