Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន   អាយ៉ាត់:
وَيُكَلِّمُ ٱلنَّاسَ فِي ٱلۡمَهۡدِ وَكَهۡلٗا وَمِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
46. «እርሱም ገና በህፃንነቱ ካደገም በኋላ ሰዎችን ያነጋግራል:: ከመልካሞቹም አንዱ ነው።» (አላት)።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَتۡ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٞ وَلَمۡ يَمۡسَسۡنِي بَشَرٞۖ قَالَ كَذَٰلِكِ ٱللَّهُ يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُۚ إِذَا قَضَىٰٓ أَمۡرٗا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ
47. እርሷም «ጌታዬ ሆይ! ማንም ሰው በትዳርም ሆነ በዝሙት ሳይነካኝ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለች:: መልአኩ ጅብሪልም አላት: «እነደዚሁ ነው። አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል። የአንድን ነገር መሆን በፈለገ ጊዜ የሚለው ‹ሁን› ብቻ ነው። ወዲያውኑም ያ ነገር ይሆናል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيُعَلِّمُهُ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَٱلتَّوۡرَىٰةَ وَٱلۡإِنجِيلَ
48. «ጽሕፈትንና ጥበብን፤ ተውራትንና ኢንጂልንም ያስተምረዋል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ أَنِّي قَدۡ جِئۡتُكُم بِـَٔايَةٖ مِّن رَّبِّكُمۡ أَنِّيٓ أَخۡلُقُ لَكُم مِّنَ ٱلطِّينِ كَهَيۡـَٔةِ ٱلطَّيۡرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيۡرَۢا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۖ وَأُبۡرِئُ ٱلۡأَكۡمَهَ وَٱلۡأَبۡرَصَ وَأُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۖ وَأُنَبِّئُكُم بِمَا تَأۡكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِي بُيُوتِكُمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗ لَّكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ
49.«ወደ ኢስራኢል ልጆችም መልዕክተኛ ያደርገዋል። ይላልም: ›, ‹እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዐምር መጣሁላችሁ:: እኔ ለእናንተ ከጭቃ የወፍ ቅርጽ አይነት እፈጥራለሁ:: በእርሱም እተነፍስበታለሁ:: ከዚያም በአላህ ፈቃድ ወፍ ይሆናል:: እውር ሆኖ የተወለደንም ለምጸኛንም በአላህ ፈቃድ አድናለሁ:: ሙታንንም በአላህ ፍቃድ አስነሳለሁ:: የምትበሉትንና በየቤቶቻችሁ የምታደልቡትን ሁሉ እነግራችኋለሁ:: (መረጃዎችን አገናዝባችሁ) የምታምኑ እንደሆናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ ግልጽ ተዐምር አለበት።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمُصَدِّقٗا لِّمَا بَيۡنَ يَدَيَّ مِنَ ٱلتَّوۡرَىٰةِ وَلِأُحِلَّ لَكُم بَعۡضَ ٱلَّذِي حُرِّمَ عَلَيۡكُمۡۚ وَجِئۡتُكُم بِـَٔايَةٖ مِّن رَّبِّكُمۡ فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُونِ
50.«‹ከእኔ በፊት የነበረውን ተውራትን ያረጋገጥኩ ስሆን ያንም በእናንተ ላይ እርም የተደረገውን ነገር ከፊሉን ለእናንተ እፈቅድ ዘንድ መጣሁላችሁ:: ከጌታችሁም በሆነ ተዐምር መጣሁላችሁ:: አላህን ፍሩ:: እኔንም ታዘዙኝ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمۡ فَٱعۡبُدُوهُۚ هَٰذَا صِرَٰطٞ مُّسۡتَقِيمٞ
51.«‹አላህ ጌታዬ የእናንተም ጌታችሁ ነው:: ስለዚህ በብቸኝነት ተገዙት:: ይህ ቀጥተኛው መንገድ ነው።› ይላቸዋል»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنۡهُمُ ٱلۡكُفۡرَ قَالَ مَنۡ أَنصَارِيٓ إِلَى ٱللَّهِۖ قَالَ ٱلۡحَوَارِيُّونَ نَحۡنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشۡهَدۡ بِأَنَّا مُسۡلِمُونَ
52. ዒሳ ከእነርሱ ክህደት በተሰማው ጊዜ፡- «ወደ አላህ የእኔ ረዳቶች የሚሆኑ እነማን ናቸው?» አለ:: ሀዋርያትም አሉ፡- «ዒሳ ሆይ! እኛ የአላህ ረዳቶች ነን:: በአላህ አምነናል:: ትክክለኛና ታዛዦች መሆናችንን መስክር።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ