Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ពាក៏រ៉ោះ   អាយ៉ាត់:
وَقَالَتِ ٱلۡيَهُودُ لَيۡسَتِ ٱلنَّصَٰرَىٰ عَلَىٰ شَيۡءٖ وَقَالَتِ ٱلنَّصَٰرَىٰ لَيۡسَتِ ٱلۡيَهُودُ عَلَىٰ شَيۡءٖ وَهُمۡ يَتۡلُونَ ٱلۡكِتَٰبَۗ كَذَٰلِكَ قَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَ مِثۡلَ قَوۡلِهِمۡۚ فَٱللَّهُ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فِيمَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ
113. እነርሱ መጽሐፉን የሚያነቡ ሲሆን አይሁድ «ክርስቲያኖች በምንም ላይ አይደሉም።» አሉ:: ክርስቲያኖችም «አይሁዶች በምንም ላይ አይደሉም።» አሉ። እንደዚሁ እነዚያ የማያውቁት አጋሪዎችም የነሱን ተመሳሳይ ንግግር ተናገሩ:: አላህ በዚያ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ላይ ሁሉ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّن مَّنَعَ مَسَٰجِدَ ٱللَّهِ أَن يُذۡكَرَ فِيهَا ٱسۡمُهُۥ وَسَعَىٰ فِي خَرَابِهَآۚ أُوْلَٰٓئِكَ مَا كَانَ لَهُمۡ أَن يَدۡخُلُوهَآ إِلَّا خَآئِفِينَۚ لَهُمۡ فِي ٱلدُّنۡيَا خِزۡيٞ وَلَهُمۡ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٞ
114. የአላህን መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳበት ከከለከለና መስጊዶችንም ለማበላሸት ከጣረ ይበልጥ ድንበር አላፊ (አጥፊ) ማን ነው? እነዚያ በፍርሃት ተውጠው እንጂ ወደ መስጊዶች ሊገቡ አይገባቸዉም። ለነርሱም በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አለባቸው:: በመጨረሻይቱ ሀገርም ታላቅ ቅጣት አለባቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلِلَّهِ ٱلۡمَشۡرِقُ وَٱلۡمَغۡرِبُۚ فَأَيۡنَمَا تُوَلُّواْ فَثَمَّ وَجۡهُ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ وَٰسِعٌ عَلِيمٞ
115. ምስራቁም ምዕራቡም የአላህ ብቻ ነው:: በአላህ ትእዛዝ (ፊቶቻችሁን) ለሶላት ወደ የትም አቅጣጫ ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ዘንድ ነው:: አላህ በእርግጥ ችሮታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነዉና፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدٗاۗ سُبۡحَٰنَهُۥۖ بَل لَّهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ كُلّٞ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
116. አላህ «ልጅ አለው።» አሉ:: ከሚሉት ጥራት ተገባው:: ይልቁንም በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው:: ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
بَدِيعُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ وَإِذَا قَضَىٰٓ أَمۡرٗا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ
117. ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው:: ማንንም ነገር ማስገኘት በፈለገ ጊዜ ለእርሱ የሚለው ‹‹ሁን›› ብቻ ነው:: ወዲያዉም እንዳለው ይሆናል፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَ لَوۡلَا يُكَلِّمُنَا ٱللَّهُ أَوۡ تَأۡتِينَآ ءَايَةٞۗ كَذَٰلِكَ قَالَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِم مِّثۡلَ قَوۡلِهِمۡۘ تَشَٰبَهَتۡ قُلُوبُهُمۡۗ قَدۡ بَيَّنَّا ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يُوقِنُونَ
118. እነዚያ የማያውቁት «(አንተ መልዕክተኛ ስለመሆንህ) አላህ ለምን አያናግረንም? ወይም (ለእውነተኛነትህ) ተዓምር አይመጣልንም ኖሯልን? አሉ:: እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩትም ልክ እንደዚሁ ንግግራቸው ብጤ ብለዋል:: ልቦቻቸው በክህደት ተመሳሰሉ:: ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ አናቅጽን በእርግጥ አብራርተናል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّآ أَرۡسَلۡنَٰكَ بِٱلۡحَقِّ بَشِيرٗا وَنَذِيرٗاۖ وَلَا تُسۡـَٔلُ عَنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلۡجَحِيمِ
119. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርገን በእውነት ላክንህ:: ከእሳት ጓዶችም ሁኔታ አትጠየቅም፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ពាក៏រ៉ោះ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ