Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ពាក៏រ៉ោះ   អាយ៉ាត់:
وَٱقۡتُلُوهُمۡ حَيۡثُ ثَقِفۡتُمُوهُمۡ وَأَخۡرِجُوهُم مِّنۡ حَيۡثُ أَخۡرَجُوكُمۡۚ وَٱلۡفِتۡنَةُ أَشَدُّ مِنَ ٱلۡقَتۡلِۚ وَلَا تُقَٰتِلُوهُمۡ عِندَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ حَتَّىٰ يُقَٰتِلُوكُمۡ فِيهِۖ فَإِن قَٰتَلُوكُمۡ فَٱقۡتُلُوهُمۡۗ كَذَٰلِكَ جَزَآءُ ٱلۡكَٰفِرِينَ
191. ባገኛችኃቸዉም ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው:: ካስወጧችሁም ስፍራ አስወጧቸው:: ፈተና (ሁክት) ከመግደል የከፋ ነውና:: በተከበረው መስጊድም ዘንድ በእርሱ ውስጥ እስከሚጋደሏችሁ ድረስ በእርሱ ውስጥ አትጋደሏቸው:: ከተጋደሏችሁ ግን ግደሏቸው:: የከሓዲያን ቅጣት ልክ እንደዚህ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَإِنِ ٱنتَهَوۡاْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ
192. ከውጊያ ከታቀቡ ግን አላህ መሀሪና አዛኝ ነው፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَٰتِلُوهُمۡ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتۡنَةٞ وَيَكُونَ ٱلدِّينُ لِلَّهِۖ فَإِنِ ٱنتَهَوۡاْ فَلَا عُدۡوَٰنَ إِلَّا عَلَى ٱلظَّٰلِمِينَ
193. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ፈተና (ሁከት) እስኪወገድና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስኪሆን ድረስ ተጋደሏቸው:: ከታቀቡ ግን የሀይል እርምጃ ድንበርን ባለፉ ላይ እንጂ (በሰላማዊ ላይ) አይጸናም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱلشَّهۡرُ ٱلۡحَرَامُ بِٱلشَّهۡرِ ٱلۡحَرَامِ وَٱلۡحُرُمَٰتُ قِصَاصٞۚ فَمَنِ ٱعۡتَدَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَٱعۡتَدُواْ عَلَيۡهِ بِمِثۡلِ مَا ٱعۡتَدَىٰ عَلَيۡكُمۡۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلۡمُتَّقِينَ
194. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) የተከበረው ወር በተከበረው ወር አንፃር ነው::ክብሮችም ሁሉ ተመሳሳዮች ናቸው፡፡ (ፍትሃዊ አጸፋዊ እርምጃ የተከበረን ህግ በጣሱ ላይ ተደንግጓል):: ወሰን ያለፈባችሁን በእናንተ ወሰን ባለፈው ቢጤ ወሰን ያለፈውን ያህል በእርሱም ላይ ወሰን እለፉበት:: አላህንም ፍሩ:: አላህ እርሱን ከሚፈሩት ጋር መሆኑንም እወቁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَنفِقُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلَا تُلۡقُواْ بِأَيۡدِيكُمۡ إِلَى ٱلتَّهۡلُكَةِ وَأَحۡسِنُوٓاْۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
195. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በአላህ መንገድ ላይ ለግሱ:: ራሳችሁንም በገዛ እጃችሁ ለጥፋት አትዳርጉ:: በበጎ ስራም ላይ ጽኑ:: አላህ በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ይወዳልና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَتِمُّواْ ٱلۡحَجَّ وَٱلۡعُمۡرَةَ لِلَّهِۚ فَإِنۡ أُحۡصِرۡتُمۡ فَمَا ٱسۡتَيۡسَرَ مِنَ ٱلۡهَدۡيِۖ وَلَا تَحۡلِقُواْ رُءُوسَكُمۡ حَتَّىٰ يَبۡلُغَ ٱلۡهَدۡيُ مَحِلَّهُۥۚ فَمَن كَانَ مِنكُم مَّرِيضًا أَوۡ بِهِۦٓ أَذٗى مِّن رَّأۡسِهِۦ فَفِدۡيَةٞ مِّن صِيَامٍ أَوۡ صَدَقَةٍ أَوۡ نُسُكٖۚ فَإِذَآ أَمِنتُمۡ فَمَن تَمَتَّعَ بِٱلۡعُمۡرَةِ إِلَى ٱلۡحَجِّ فَمَا ٱسۡتَيۡسَرَ مِنَ ٱلۡهَدۡيِۚ فَمَن لَّمۡ يَجِدۡ فَصِيَامُ ثَلَٰثَةِ أَيَّامٖ فِي ٱلۡحَجِّ وَسَبۡعَةٍ إِذَا رَجَعۡتُمۡۗ تِلۡكَ عَشَرَةٞ كَامِلَةٞۗ ذَٰلِكَ لِمَن لَّمۡ يَكُنۡ أَهۡلُهُۥ حَاضِرِي ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ
196. ሐጅንና ዑምራን ለአላህ ብቻ ብላችሁ በትክክል ፈጽሙ:: ከጀመራችሁ በኋላ ብትታጉዱም ከመስዋአት የቻላችሁትን መሰዋት አለባችሁ:: መስዋእቱ ከመታረጃው ስፍራ እስኪደርስ ድረስም ራሶቻችሁን አትላጩ:: ከናንተም ውስጥ በሐጅ ላይ ሁኖ የታመመ ወይም በራስ ቅሉ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሰው ቢላጭ ከመፆም ወይም መስዋዕትን ቤዛ መስጠት አለበት:: ጸጥታም ባገኛችሁ ጊዜ እስከ ሐጅ መፈጸሚያ ቀን ድረስ በዑምራ አስቀድሞ በመፈጸም የተገላገለ ሰው ከመስዋእቱ የተገራውን (የቻለዉን) መሰዋት አለበት:: ያላገኘም ሰው ሶስትን ቀናት በሐጅ (ወራት) ላይ ሰባትንም ቀናት ደግሞ በተመለሳችሁ ጊዜ መፆም አለበት:: እነዚህ ሙሉ አስር (ቀናት) ናቸው:: ይህም (ህግ) ቤተሰቦቹ ከቅዱሱ መስጊድ አቅራቢያ ላልሆኑ ነው:: አላህንም ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ መሆኑንም እወቁ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ពាក៏រ៉ោះ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ