Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ


ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ពាក៏រ៉ោះ   អាយ៉ាត់:
مَثَلُهُمۡ كَمَثَلِ ٱلَّذِي ٱسۡتَوۡقَدَ نَارٗا فَلَمَّآ أَضَآءَتۡ مَا حَوۡلَهُۥ ذَهَبَ ٱللَّهُ بِنُورِهِمۡ وَتَرَكَهُمۡ فِي ظُلُمَٰتٖ لَّا يُبۡصِرُونَ
17. የእነርሱ ንፍቅና ምሳሌ ልክ እንደዚያ እሳትን እንዳነደደና ከዚያ በዙሪያው ያለውን ሁሉ ባበራችለት ጊዜ አላህ ብርሃናቸውን እንደወሰደባቸው እና በጨለማዎች ውስጥ የማያዩ ሆነው እንደተዋቸው ብጤ ነው፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
صُمُّۢ بُكۡمٌ عُمۡيٞ فَهُمۡ لَا يَرۡجِعُونَ
18. እነርሱ (ሓቅን የማይሰሙ) ደንቆሮዎች፤ (ሓቅን የማይናገሩ) ዲዳዎች፤ (ሓቅን የማያዩ) እውሮች ናቸው:: ስለዚህ እነርሱ (ከስህተት) አይመለሱም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَوۡ كَصَيِّبٖ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فِيهِ ظُلُمَٰتٞ وَرَعۡدٞ وَبَرۡقٞ يَجۡعَلُونَ أَصَٰبِعَهُمۡ فِيٓ ءَاذَانِهِم مِّنَ ٱلصَّوَٰعِقِ حَذَرَ ٱلۡمَوۡتِۚ وَٱللَّهُ مُحِيطُۢ بِٱلۡكَٰفِرِينَ
19. ወይም (ምሳሌያቸው) ከሰማይ እንደወረደ ዝናብ (ባለቤቶች) ነው:: በእርሱ (በደመናው) ውስጥ ጨለማዎች፤ ነጎድጓድና ብልጭታ ያሉበት ሲሆን ከመብረቆቹ ሊመጣ ከሚችል ጥቃት ሞትን በመፍራት ጣቶቻቸውን በጆሮዎቻቸው ውስጥ እንደሚያደርጉ ሰዎች ቢጤ ነው:: አላህ ከሓዲያንን (በእውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَكَادُ ٱلۡبَرۡقُ يَخۡطَفُ أَبۡصَٰرَهُمۡۖ كُلَّمَآ أَضَآءَ لَهُم مَّشَوۡاْ فِيهِ وَإِذَآ أَظۡلَمَ عَلَيۡهِمۡ قَامُواْۚ وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَذَهَبَ بِسَمۡعِهِمۡ وَأَبۡصَٰرِهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
20 ብልጭታው ዓይኖቻቸውን ሊነጥቅ ይቀርባል:: ለእነርሱ ባበራላቸው ቁጥር በውስጡ ይሄዳሉ:: በእነርሱም ላይ ባጨለመባቸው ጊዜ ደግሞ ይቆማሉ:: አላህ በፈለገ ኖሮ መስሚያዎቻቸውንና ማያዎቻቸውን ይወስድባቸው ነበር:: አላህ በነገሮች ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱعۡبُدُواْ رَبَّكُمُ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ وَٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ
21. እናንተ ሰዎች ሆይ! ያን እናንተንና እነዚያን ከናንተ በፊት የነበሩትን የፈጠረውን ጌታችሁን (አላህን) በብቸኝነት ተገዙት:: ቅጣትን ልትጠነቀቁ ዘንድ፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ فِرَٰشٗا وَٱلسَّمَآءَ بِنَآءٗ وَأَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجَ بِهِۦ مِنَ ٱلثَّمَرَٰتِ رِزۡقٗا لَّكُمۡۖ فَلَا تَجۡعَلُواْ لِلَّهِ أَندَادٗا وَأَنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
22. እርሱ (አላህ) ያ ለእናንተ ምድርን ምንጣፍ፤ ሰማይን ጣራ ያደረገ ጌታ ነው::ከሰማይ ዳመና ውሃን ያወረደና ከዚያ በውሃው ከፍሬዎች ሁሉ ለእናንተ ሲሳይን ያወጣላችሁ ነው:: እናም (ብቸኛ ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትሆኑ ለአላህ (በአምልኮ) አጋሮችን አታድርጉ፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِن كُنتُمۡ فِي رَيۡبٖ مِّمَّا نَزَّلۡنَا عَلَىٰ عَبۡدِنَا فَأۡتُواْ بِسُورَةٖ مِّن مِّثۡلِهِۦ وَٱدۡعُواْ شُهَدَآءَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
23. (እናንተ ሰዎች ሆይ!) በአገልጋያችን (በሙሐመድ) ላይ ባወረድነው (ቁርኣን) በመጠራጠር ላይ ከሆናችሁም ከእርሱ ጋር ሊወዳደር የሚችል አንድ ምዕራፍ እንኳን እስቲ አምጡ:: እውነተኞች እንደሆናችሁ ከአላህ ሌላ ረዳቶቻችሁንም ሁሉ ጥሩ፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَإِن لَّمۡ تَفۡعَلُواْ وَلَن تَفۡعَلُواْ فَٱتَّقُواْ ٱلنَّارَ ٱلَّتِي وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلۡحِجَارَةُۖ أُعِدَّتۡ لِلۡكَٰفِرِينَ
24. (ይህንን) ባትሰሩ ግን በርግጥም አትሰሩትምና (አትፈጽሙትምና) ከዚያች መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች ከሆነው ከገሀነም እሳት ራሳችሁን ጠብቁ:: ለከሓዲያን ሁሉ ተደግሳለችና፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ពាក៏រ៉ោះ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ