Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ពាក៏រ៉ោះ   អាយ៉ាត់:
وَإِذۡ قَالَ رَبُّكَ لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ إِنِّي جَاعِلٞ فِي ٱلۡأَرۡضِ خَلِيفَةٗۖ قَالُوٓاْ أَتَجۡعَلُ فِيهَا مَن يُفۡسِدُ فِيهَا وَيَسۡفِكُ ٱلدِّمَآءَ وَنَحۡنُ نُسَبِّحُ بِحَمۡدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَۖ قَالَ إِنِّيٓ أَعۡلَمُ مَا لَا تَعۡلَمُونَ
30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ለመላዕክት «እኔ በምድር ላይ (ምትክ) ወኪል ላደርግ ነው።» ባለ ጊዜ (የሆነውን ለህዝቦችህ አስታውስ)። «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ፤ የምናሞግስህ ስንሆን በምድር ውስጥ የሚያጠፉትንና ደሞችንም የሚያፈሱትን ታደርጋለህን?» አሉ:: አላህም «እኔ እናንተ የማታውቁትን ነገር ሁሉ አውቃለሁ» አላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَعَلَّمَ ءَادَمَ ٱلۡأَسۡمَآءَ كُلَّهَا ثُمَّ عَرَضَهُمۡ عَلَى ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ فَقَالَ أَنۢبِـُٔونِي بِأَسۡمَآءِ هَٰٓؤُلَآءِ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
31. ለአደምም ስሞችን ሁሉ አስተማረው:: ከዚያም በመላዕክት ላይ (ተሰያሚዎቹን) አቀረባቸው። «እውነተኞች ከሆናችሁ የእነዚህን ተሰያሚዎች መጠሪያ ንገሩኝ?» አላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالُواْ سُبۡحَٰنَكَ لَا عِلۡمَ لَنَآ إِلَّا مَا عَلَّمۡتَنَآۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡحَكِيمُ
32. እነርሱም «ጥራት ይገባህ አንተ ካስተማርከን ነገር በስተቀር እኛ ምንም እውቀት የለንም:: አንተ ብቸኛው ጥበበኛና አዋቂው ነህና›› አሉ፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ يَٰٓـَٔادَمُ أَنۢبِئۡهُم بِأَسۡمَآئِهِمۡۖ فَلَمَّآ أَنۢبَأَهُم بِأَسۡمَآئِهِمۡ قَالَ أَلَمۡ أَقُل لَّكُمۡ إِنِّيٓ أَعۡلَمُ غَيۡبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَأَعۡلَمُ مَا تُبۡدُونَ وَمَا كُنتُمۡ تَكۡتُمُونَ
33. አላህም «አደም ሆይ! ስሞቻቸውን ንገራቸው።» አለው። ከዚያም ስሞቻቸውን በነገራቸው ጊዜ «እኔ የሰማያትንና የምድርን ሩቅ ምስጢር አውቃለሁ። የምትገልጹትንና ያንንም ትደብቁት የነበራችሁትን ሁሉ አውቃለሁ አላልኳችሁምን?» አላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ أَبَىٰ وَٱسۡتَكۡبَرَ وَكَانَ مِنَ ٱلۡكَٰفِرِينَ
34. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መላዕክትን «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ከዲያብሎስ በቀር መላዕክት ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ። እርሱማ እምቢ አለ። ኮራም። ከከሓዲያንም ሆነ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقُلۡنَا يَٰٓـَٔادَمُ ٱسۡكُنۡ أَنتَ وَزَوۡجُكَ ٱلۡجَنَّةَ وَكُلَا مِنۡهَا رَغَدًا حَيۡثُ شِئۡتُمَا وَلَا تَقۡرَبَا هَٰذِهِ ٱلشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
35. «አደም ሆይ! አንተና ሚስትህ በገነት ውስጥ ተቀመጡ:: በእርሷም ዉስጥ በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ:: ግን ከበደለኞች ትሆናላችሁና ይህችን ዛፍ አትቅረቡ።» አልናቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَأَزَلَّهُمَا ٱلشَّيۡطَٰنُ عَنۡهَا فَأَخۡرَجَهُمَا مِمَّا كَانَا فِيهِۖ وَقُلۡنَا ٱهۡبِطُواْ بَعۡضُكُمۡ لِبَعۡضٍ عَدُوّٞۖ وَلَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ مُسۡتَقَرّٞ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٖ
36. ሰይጣንም ከእርሷ አሳሳታቸው። ከነበሩበትም ገነት አወጣቸው። «ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲሆን ሁላችሁም (ወደ ምድር) ውረዱ። ለእናንተም በምድር ላይ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ።» አልናቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَتَلَقَّىٰٓ ءَادَمُ مِن رَّبِّهِۦ كَلِمَٰتٖ فَتَابَ عَلَيۡهِۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ
37. ከዚያም አደም ከጌታው የመታረቂያ ቃል ተማረ:: ጌታዉም ተማጽኖውን ተቀበለው:: አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ពាក៏រ៉ោះ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ