Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ


ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ពាក៏រ៉ោះ   អាយ៉ាត់:
ٱلَّذِينَ يَأۡكُلُونَ ٱلرِّبَوٰاْ لَا يَقُومُونَ إِلَّا كَمَا يَقُومُ ٱلَّذِي يَتَخَبَّطُهُ ٱلشَّيۡطَٰنُ مِنَ ٱلۡمَسِّۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَالُوٓاْ إِنَّمَا ٱلۡبَيۡعُ مِثۡلُ ٱلرِّبَوٰاْۗ وَأَحَلَّ ٱللَّهُ ٱلۡبَيۡعَ وَحَرَّمَ ٱلرِّبَوٰاْۚ فَمَن جَآءَهُۥ مَوۡعِظَةٞ مِّن رَّبِّهِۦ فَٱنتَهَىٰ فَلَهُۥ مَا سَلَفَ وَأَمۡرُهُۥٓ إِلَى ٱللَّهِۖ وَمَنۡ عَادَ فَأُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِۖ هُمۡ فِيهَا خَٰلِدُونَ
275. እነዚያ አራጣን የሚበሉ ሁሉ ያ ሰይጣን ሰፍኖበት ራሱን የሚስት ሰው ከአውድቅቱ እንደሚነሳ አይነት ሁነው እንጂ ከመቃብራቸው አይነሱም:: ይህም የሆነው እነርሱ መሸጥ ልክ እንደ አራጣ ነው በማለታቸው ነው:: አላህ ግን መሸጥን ፈቅዷል:: አራጣን እርም አድርጓል:: ከጌታው ግሳጼ የመጣለት እና ከዚያ የተከለከለ ሰው ሁሉ ከዚህ አዋጅ በፊት ያካበተውን እንደያዘ መቆየት ይችላል:: የወደፊት እጣፈንታው ወደ አላህ ነው:: አራጣን ወደ መብላት የተመለሱ ሰዎች እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው:: እነርሱ በውስጧ ዘወታሪዎች ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَمۡحَقُ ٱللَّهُ ٱلرِّبَوٰاْ وَيُرۡبِي ٱلصَّدَقَٰتِۗ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ كُلَّ كَفَّارٍ أَثِيمٍ
276. አላህ የአራጣን ገንዘብ ያከስማል (በረከቱን ያጠፋል):: መልካም ልገሳዎችን ያፋፋል:: አላህም ኃጢአተኛንና ከሓዲን ሁሉ አይወድምና፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَوُاْ ٱلزَّكَوٰةَ لَهُمۡ أَجۡرُهُمۡ عِندَ رَبِّهِمۡ وَلَا خَوۡفٌ عَلَيۡهِمۡ وَلَا هُمۡ يَحۡزَنُونَ
277. እነዚያ ያመኑና መልካም ስራዎችንም የሰሩ፤ ሶላትን አስተካክለው የሰገዱና ዘካንም የሰጡ እነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፤ በእነርሱም ላይ ምንም ይደርስብናል ብለው ፍርሀት የለባቸዉም:: ምንም ነገር ያመልጠናል ብለው አያዝኑምም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَذَرُواْ مَا بَقِيَ مِنَ ٱلرِّبَوٰٓاْ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ
278. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ:: ከአራጣም የቀረውን አትውሰዱ:: ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ (ተጠንቀቁ)::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَإِن لَّمۡ تَفۡعَلُواْ فَأۡذَنُواْ بِحَرۡبٖ مِّنَ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۖ وَإِن تُبۡتُمۡ فَلَكُمۡ رُءُوسُ أَمۡوَٰلِكُمۡ لَا تَظۡلِمُونَ وَلَا تُظۡلَمُونَ
279. የታዘዛችሁትን ባትሰሩ ከአላህና ከመልዕክተኛ ጦርነት ታውጆባችኋል:: ከወለዳዊ ድርጊታችሁ ብትታቀቡ ግን አንጡራ ገንዘባችሁ ለእናንተው እንደተጠበቀ ነው:: ሌሎችን አትበድሉም አትበደሉምም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِن كَانَ ذُو عُسۡرَةٖ فَنَظِرَةٌ إِلَىٰ مَيۡسَرَةٖۚ وَأَن تَصَدَّقُواْ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُمۡ تَعۡلَمُونَ
280. የድህነት ባለቤት ባለዕዳ ሰው ቢኖር ገንዘብ እስኪያገኝ ድረስ ማቆየት ነው:: (የእፎይታ ጊዜ ይሰጠው) ስጡት:: እዳውን በበጎ አድራጊነት ሙሉ በሙሉ ብትሰርዙለትም ለእናንተ በላጭ ነው። የምታውቁ ብትሆኑ (ትሰሩታላችሁ)::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱتَّقُواْ يَوۡمٗا تُرۡجَعُونَ فِيهِ إِلَى ٱللَّهِۖ ثُمَّ تُوَفَّىٰ كُلُّ نَفۡسٖ مَّا كَسَبَتۡ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
281. ያን ወደ አላህ የምትመለሱበትን ቀን ፍሩ:: ሁሉም ነፍስ ያኔ ከሰራቸው አኳያ ዋጋዋን ታገኛለች:: በዚያ ዕለት (በሱ ዉስጥ) ተበዳይ ወገኖች ፈጽሞ አይኖሩም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ពាក៏រ៉ោះ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ